Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 45:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በጨለማና በድብቅ ቦታ የተከማቸውን ሀብት እሰጥሃለሁ። በዚህም በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንኩ ታውቃለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ፣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቅ ዘንድ፣ በተሰወረ ስፍራ የተከማቸውን ሀብት፣ በጨለማም ያለውን ንብረት እሰጥሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እኔ እንደሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በስ​ም​ህም የም​ጠ​ራህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨ​ለማ የነ​በ​ሩ​ትን መዛ​ግ​ብት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ የማ​ይ​ታ​የ​ው​ንም የተ​ደ​በ​ቀ​ውን ሀብት እገ​ል​ጥ​ል​ሃ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 45:3
15 交叉引用  

እንግዲህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአገልጋይህ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ሁሉ እንዲፈጸም አድርግልኝ።


የፋርስ ንጉሠ ነገሥትም በዐዋጅ የሰጠው ትእዛዝ እንዲህ የሚል ነበር፦ “የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የዓለም ሁሉ ገዢ አድርጎኛል፤ እርሱም ቤተ መቅደስን በይሁዳ ምድር በምትገኘው በኢየሩሳሌም እንድሠራለት አዞኛል።


ሙሴም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፦ “ይህን ሕዝብ ወደዚያች ምድር መርቼ እንድወስድ አዝዘኸኛል፤ ነገር ግን ከእኔ ጋር ማንን እንደምትልክ አልነገርከኝም፤ እኔን እንደምታውቀኝና በእኔም ደስ እንደሚልህ ገልጠህልኛል፤


እግዚአብሔርም ሙሴን “እኔ አንተን በሚገባ በትክክል ስለማውቅህና በአንተም ደስ ስለምሰኝ የምትለውን ሁሉ አደርጋለሁ” አለው።


እናንተም አማልክት መሆናችሁን እንድናውቅ ወደ ፊት የሚሆነውን ሁሉ እስቲ ንገሩን፤ እስቲ መልካም ነገርን አድርጉ፤ ወይም አይተንላችሁ በመፍራት እንድንሸበር ክፉ ነገርን ለማድረስ ሞክሩ።


የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! የፈጠራችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የታደግኋችሁ ስለ ሆነ አትፍሩ፤ እናንተ የእኔ ናችሁ፤ በስማችሁም ጠርቼአችኋለሁ።


እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ ጠርቼዋለሁም፤ እኔ አመጣዋለሁ፤ የእርሱም ተልእኮ የተሳካ ይሆናል።


በደሴት የምትኖሩ ሕዝቦች አድምጡኝ! በሩቅ አገር ያላችሁም ሰዎች አስተውሉ፤ እግዚአብሔር ከመወለዴ በፊት ጠራኝ፤ በእናቴ ማሕፀን እያለሁ ስም አወጣልኝ።


ከእነዚያ ሰማኒያ ሰዎች መካከል በተለይ ዐሥሩ ሰዎች “እባክህ አትግደለን! እኛ በእርሻ ውስጥ የደበቅነው ብዙ ስንዴ፥ ገብስ፥ የወይራ ዘይትና ማር. አለን” ብለው እስማኤልን ለመኑት። እርሱም ምሕረት አደረገላቸው።


ከየአቅጣጫው ዝመቱባት፤ እህልዋ የተከማቸበትን ጐተራ ሁሉ ክፈቱ፤ ምርኮውንም እንደ እህል ምርት ቈልሉት፤ ምንም ነገር ሳትተዉ አገሪቱን አጥፉ!


በፈረሶቻቸው፥ በሠረገሎቻቸውና በቅጥር ወታደሮቻቸው ላይ ሰይፍ ይመዘዝ! እነርሱም እንደ ሴቶች ይሁኑ፤ በሀብታሞቹ ላይ ሰይፍ መዛችሁ ሀብታቸውን ሁሉ ዝረፉ!


አንቺ በታላላቅ ወንዞች አጠገብ የምትኖሪ ሀብታሚቱ ባቢሎን ሆይ! የተወሰነብሽ የመጥፊያሽ ዘመን ደርሶአል።


ባቢሎን ወደ ሰማይ ብትወጣ ከፍተኛውን ምሽግዋን ብታጠናክር እንኳ የሚደመስሳትን አጥፊ እልካለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


跟着我们:

广告


广告