ኢሳይያስ 45:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ሕዝቦች በሥልጣኑ ሥር እንዲገዙ ለማድረግ፥ ነገሥታትን ከሥልጣን እንዲያወርድ፥ የከተሞችን ቅጽር በሮች ይከፍትለት ዘንድ ቀኝ እጁን ለያዘውና ቀብቶ ላነገሠው ንጉሥ ቂሮስን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፦ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 “ለቀባሁት፣ ቀኝ እጁን ለያዝሁት፣ ነገሥታትን ትጥቅ አስፈታ ዘንድ፣ ሕዝብን ሁሉ ላስገዛለት፣ ደጆች እንዳይዘጉ፣ በሮቹን በፊቱ ለምከፍትለት፣ ለቂሮስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ጌታ ለቀባው፥ አሕዛብንም በፊቱ እንዲገዙለት፥ የነገሥታትንም ወገብ እዲፈታ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹ በፊቱ እንዲከፈቱለት፥ ቀኝ እጁን ለያዘው ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እግዚአብሔር አምላክ ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ኀይል እጥል ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 እግዚአብሔር ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦ 参见章节 |