Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 44:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “የዚህን እንጨት ግማሹን አነደድኩት፤ በፍሙም ዳቦ ጋገርኩበት፤ ሥጋም ጠብሼበት በላሁ፤ አሁን እንግዲህ ቀሪውን ቊራጭ እንጨት ለጣዖት ላውለውን? በአንድ ቊራጭ እንጨት ፊት ወድቄ ልስገድን?” ብሎ የሚያስብ ዕውቀት ወይም ማስተዋል ያለው አንድም ሰው የለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ማንም ቆም ብሎ አላሰበም፤ ዕውቀት ወይም ማስተዋል ስለሌለው እንዲህ ማለት አልቻለም፤ “ግማሹን በእሳት አቃጥዬዋለሁ፤ በፍሙ እንጀራ ጋግሬበታለሁ፤ ሥጋ ጠብሼበት በልቻለሁ፤ ታዲያ፣ በቀረው እንዴት ጸያፍ ነገር እሠራለሁ? ለግንድስ መስገድ ይገባኛልን?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በልቡም ማንም አያስብም፦ “ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፤ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን?” ለማለት እንኳን እውቀትና ማስተዋል የለውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ማንም በልቡ አያ​ስ​ብም፥ “ግማ​ሽ​ዋን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ያ​ለሁ፤ በፍ​ም​ዋም ላይ እን​ጀ​ራን ጋግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ሥጋም ጠብሼ በል​ቻ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ው​ንም አስ​ጸ​ያፊ ነገር አደ​ር​ጋ​ለ​ሁን? ለዛ​ፍስ ግንድ እሰ​ግ​ዳ​ለ​ሁን? እን​ዲ​ልም ዕው​ቀ​ትና ማስ​ተ​ዋል የለ​ውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በልቡም ማንም አያስብም፦ ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፥ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም እውቀትና ማስተዋል የለውም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 44:19
16 交叉引用  

የሲዶናውያን ሴት አምላክ ለነበረችው ለዐስታሮትና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለአጸያፊው ለዐሞናውያን አምላክ ሰገደ።


ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ አጸያፊዎች ለሆኑት ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን አዘጋጀላቸው።


እንዲሁም ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከርኲሰት ተራራ በስተ ደቡብ ዐስታሮት ተብላ ለምትጠራው ለሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአብ አምላክና ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞን አምላክ ንጉሥ ሰሎሞን አሠርቶአቸው የነበሩት አጸያፊዎች ምስሎች ሁሉ የረከሱ መሆናቸውን አስገነዘበ።


ንጉሥ ኢዮስያስ የድንጋይ ዐምዶችን ሁሉ ሰባበረ፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውንም የሴት አምላክ ምስሎች አንከታክቶ ጣለ፤ እነርሱ ቆመውበት የነበረውንም ስፍራ የሙታን አጥንት ሞላበት።


የሆነውን ነገር ሁሉ ከቁም ነገር ሳይቈጥረው ወደ ቤተ መንግሥቱ ተመልሶ ሄደ።


እንደዚህ ያሉት ሰዎች ዐይኖቻቸው ስለ ተሸፈኑ ማየት አይችሉም።


“ከየሀገሩ ከስደት ተርፋችሁ የተመለሳችሁ፥ ተሰብስባችሁ በአንድነት ቅረቡ! የእንጨት ጣዖቶችን ይዘው የሚዘዋወሩና ማዳን ወደማይችል ጣዖት የሚጸልዩ ዕውቀት የሌላቸው ናቸው።


“እናንተ ዐመፀኞች! በአእምሮአችሁ ያዙት፤ በልባችሁም አኑሩት።


ስለዚህ ሕዝቤ ዕውቀት በማጣታቸው ተማርከው ይወሰዳሉ፤ የተከበሩ መሪዎቻቸው እስከ ሞት ድረስ ይራባሉ፤ ሕዝቡም በውሃ ጥም ይቃጠላል።


“ለእኔ በሬ ሲሠዉ በሌላ በኩል የሰውን ሕይወት ያጠፋሉ፤ ለእኔ ጠቦት ሲሠዉ ለጣዖትም ውሻ ያቀርባሉ፤ ለእኔ የእህል መሥዋዕት ሲያቀርቡ፤ የዕሪያ ደምም ለጣዖት ያቀርባሉ፤ ለእኔ ዕጣን ያጥናሉ፤ ጣዖቶቻቸውንም ያመሰግናሉ፤ የራሳቸውን አካሄድ በመምረጥ በርኲሰታቸው ይደሰታሉ።


ሰውየውም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! እዚህ ድረስ እንድትመጣ የተደረገበት ምክንያት እኔ የማሳይህን ሁሉ እንድትረዳ ስለ ሆነ ልብ ብለህ ተመልከት፤ በጥንቃቄም ስማ፤ የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ንገራቸው።”


ስለዚህ ከእንጨት የተሠራውን ጣዖት ምክር ይጠይቁታል፤ የጥንቈላ ዘንጋቸውም ለጥያቄአቸው መልስ የሚሰጥ ይመስላቸዋል፤ በዝሙት መንፈስም ተመርተው ከእግዚአብሔር ርቀዋል።


ነገር ግን እኔ ይህን ሁሉ ክፋታቸውን እንደማስታውስ ከቶ አይገነዘቡም፤ ከዚህ የተነሣ በገዛ ኃጢአታቸው ተከበዋል፤ ክፉ ሥራቸው ሁሉ ከእኔ የተሰወረ አይደለም።”


ያላችሁበትን ሁኔታ አስቡ።


“ ‘እንጨት ጠርቦ፥ ድንጋይ አለዝቦ፥ ብረት አቅልጦ ጣዖት በመሥራት በስውር የሚሰግድለት ማንኛውም ሰው የተረገመ ይሁን! እግዚአብሔር የጣዖት አምልኮን ይጠላል።’ “ሕዝቡም ሁሉ ሲመልሱ ‘አሜን!’ ይበሉ።


እርሱም እንዲህ አለ፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ መጠበቅ ይችሉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዙ እኔ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን የምሰጣችሁን ቃላት ሁሉ አስተውሉ።


跟着我们:

广告


广告