ኢሳይያስ 44:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ሰው ከአንድ ዛፍ ግማሹን ለማገዶ፥ ግማሹንም ጣዖት ለመሥራት ይጠቀምበታል፤ ግማሹን እሳት አንድዶ ለመሞቅና እንጀራ ለመጋገር ይጠቀምበታል፤ በሌላው ጒማጅ ጣዖት ሠርቶ በፊቱ እየሰገደ ያመልከዋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ሰው ለማገዶ ይጠቀምበታል፤ ከዚያም ጥቂት ወስዶ በማንደድ ይሞቀዋል፤ እንጀራም ይጋግርበታል። ከዚሁ ጠርቦ አምላክ ያበጃል፤ ያመልከዋል፤ ጣዖትን ይሠራል፤ ወድቆም ይሰግድለታል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፤ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፤ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም የተረፈውን ጣዖታትን አበጅቶ ይሰግድላቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ለሰውም ማገዶ ይሆናል፥ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፥ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፥ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል። 参见章节 |