ኢሳይያስ 43:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ሕዝቦች ሁሉ በአንድነት ይሰብሰቡ፤ ከእነርሱ መካከል የአሁንና የቀድሞዎቹን ነገሮች አስቀድሞ የተናገረና የገለጠ ማነው? እውነተኛነታቸውን ለማረጋገጥ ምስክሮቻቸውን ያምጡ። እነርሱም ሰምተው እውነት ነው ይበሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ሕዝብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰብ፤ ሰውም ይከማች፤ ከእነርሱ አስቀድሞ ይህን የነገረን፣ የቀድሞውን ነገር ያወጀልን ማን ነው? ሌሎችን ሰምተው፣ “እውነት ነው” እንዲሉ፣ ትክክለኝነታቸውም እንዲረጋገጥ ምስክሮቻቸውን ያቅርቡ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰቡ፥ ወገኖችም ይከማቹ፤ ከመካከላቸው ይህን የሚናገር፥ የቀድሞውንስ ነገር የሚያሳየን ማን ነው? እንዲጸድቁ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፥ ሰምተውም፦ “እውነት ነው” ይበሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ተሰበሰቡ፤ አለቆችም ተከማቹ፤ ይህን ማን ይናገራል? የቀድሞውንስ ማን ይነግራችኋል? ይጸድቁ ዘንድ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፤ ሰምተውም፦ እውነትን ይናገሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰቡ ወገኖችም ይከማቹ፥ ከመካከላቸው ይህን የሚናገር፥ የቀድሞውንስ ነገር የሚያሳየን ማን ነው? ይጸድቁ ዘንድ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፥ ሰምተውም፦ እውነት ነው ይበሉ። 参见章节 |