Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 43:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሠረገሎችንና ፈረሶችን፥ የጦር ሠራዊትንና ጀግኖችን ወደ ጥፋታቸው መራቸው፤ እነርሱ ወደቁ፤ ዳግመኛም አይነሡም፤ እፍ ሲሉት እንደሚጠፋ ጧፍም ሆኑ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እንደ ገና ላይነሡ እዚያው እንዲተኙ፣ እንደ ጧፍ ኵስታሪ ረግፈው እንዲጠፉ፣ ሠረገሎችንና ፈረሶችን፣ ሰራዊቱንና ደጀኑን በአንድነት ያወጣ እንዲህ ይላል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሠረገላውንና ፈረሱን ሠራዊቱንና አርበኛውን ያወጣል፥ እነርሱ ግን በአንድነት ተኝተዋል፥ አይነሡም፤ ቀርተዋል፥ እንደ ጥዋፍ ኩስታሪም ጠፍተዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰረ​ገ​ላ​ው​ንና ፈረ​ሱን ሠራ​ዊ​ቱ​ንና አር​በ​ኛ​ውን ያወ​ጣል፤ እነ​ርሱ ግን በአ​ን​ድ​ነት ተኝ​ተ​ዋል፤ አይ​ነ​ሡም፤ ቀር​ተ​ዋል፤ እንደ ጥዋፍ ኩስ​ታ​ሪም ጠፍ​ተ​ዋል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እግዚአብሔር ሰረገላውንና ፈረሱን ሠራዊቱንና አርበኛውን ያወጣል፥ እነርሱ ግን በአንድነት ተኝተዋል፥ አይነሡም፥ ቀርተዋል፥ እንደ ጥዋፍ ኩስታሪም ጠፍተዋል፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦

参见章节 复制




ኢሳይያስ 43:17
16 交叉引用  

ዙሪያዬን እንደ ንብ ከበቡኝ፤ ነገር ግን እሾኽ በእሳት እንደሚቃጠል በፍጥነት ተቃጠሉ፤ በእግዚአብሔርም ኀይል ደመሰስኳቸው።


“እስራኤላውያን በደረቅ ምድር ባሕሩን ተሻገሩ፤ የፈርዖን ፈረሶች፥ ሠረገሎችና ፈረሰኞቹ ሁሉ ወደ ባሕር በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ውሃውን መለሰባቸው።”


“የንጉሡን ሠራዊት ከነሠረገላው ወደ ባሕር ጣለ፤ ምርጥ የሆኑት የጦር አዛዦች በቀይ ባሕር ውስጥ ሰጥመው ቀሩ።


ገለባ በእሳት ብልጭታ እንደሚጋይ “ኀይለኞች ነን” የሚሉ ሰዎች ይጠፋሉ፤ እንደ ቃጠሎ እሳት በእነርሱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት የሚያቆም የለም።


ፈረሶችንና ፈረሰኞችን፥ ሠረገሎችንና በሠረገሎች ላይ የሚቀመጡትን ለመሰባበር ተጠቀምኩብሽ፤


በመንጋጋው መንጠቆ አስገብቼ በመጐተት እርሱንና ሠራዊቱን ወደ መጡበት ወደ ኋላቸው እመልሳቸዋለሁ፤ ሠራዊቱ ከፈረሶችና የጦር ልብስ ከለበሱ ፈረሰኞቹ ጋር እጅግ የበዛ ነው፤ እያንዳንዱ ወታደር ትልቅና ትንሽ ጋሻ አንግቦ ሰይፍ ታጥቆአል፤


የተቀጠቀጠ ሸንበቆ እንኳ አይሰብርም፤ የሚጤሰውንም የጥዋፍ ክር አያጠፋም፤ ይህንንም የሚያደርገው፥ ቅን ፍርድ ድል እስኪነሣ ድረስ ነው።


ባራቅም ሠረገሎቹንና ሠራዊቱን የአሕዛብ ይዞታ እስከ ሆነችው እስከ ሐሮሼት ድረስ አሳደዳቸው፤ የሲሣራም ሠራዊት በሙሉ በሰይፍ ተገደሉ፤ አንድ ሰው እንኳ አልተረፈም።


跟着我们:

广告


广告