ኢሳይያስ 39:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 በዚያም ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሄዶ “እነዚህ ሰዎች ከወዴት መጡ? ምንስ ነገሩህ?” ብሎ ጠየቀው። ሕዝቅያስም “እነርሱ የመጡት ባቢሎን ከሚባል ከሩቅ አገር ነው” ሲል መለሰለት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ መጥቶ፣ “እነዚያ ሰዎች ምን አሉህ? ወደ አንተ ዘንድ የመጡትስ ከየት ነው?” አለው። ሕዝቅያስም፣ “ወደ እኔ የመጡት ከሩቅ አገር፣ ከባቢሎን ነው” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ነቢዩም ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፦ “እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ መጡልህ?” አለው። ሕዝቅያስም፦ “ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡልኝ” አለው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ነቢዩም ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፥ “እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ መጡ?” አለው። ሕዝቅያስም፥ “ከሩቅ ሀገር ከባቢሎን መጡ” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ነቢዩም ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፦ እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ መጡልህ? አለው። ሕዝቅያስም፦ ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡልኝ አለው። 参见章节 |