Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 37:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ከዚህ በኋላ የአሦራውያን ንጉሥ ሰናክሬም ወደኋላው በማፈግፈግ ወደ ነነዌ ተመልሶ በዚያ ኖረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ስለዚህ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ነነዌም ተመልሶ በዚያ ተቀመጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 የአሦርም ንጉሥ ሰናክሬም ተነሥቶ ሄደ፤ ተመልሶም በነነዌ ተቀመጠ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ተመ​ል​ሶም በነ​ነዌ ተቀ​መጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 የአሦርም ንጉሥ ሰናክሬም ተነሥቶ ሄደ፥ ተመልሶም በነነዌ ተቀመጠ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 37:37
15 交叉引用  

ንጉሥ ሕዝቅያስ ይህን ሁሉ በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለብሶም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሄደ፤


ንጉሥ ሕዝቅያስ እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል ብዙ ነገሮችን ካከናወነ በኋላ፥ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሰናክሬም ይሁዳን ወረረ፤ እንደሚያሸንፍ ተማምኖ የተመሸጉትን ከተሞች ከበበ


ከዚያ በኋላ አሦራውያን የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃሉ።


ሽብር በተነሣ ጊዜ ምሽጋቸው ይፈርሳል፤ የጦር መኰንኖቻቸውም አርማቸውን ትተው በመርበድበድ ይሸሻሉ”። እሳቱ በጽዮን፥ እቶኑ በኢየሩሳሌም የሆነው እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።


እናንተ ልታስተውሉትና ልትረዱት በማትችሉት ቋንቋ የሚንተባተቡባችሁን እብሪተኞች ባዕዳን ሕዝቦችን ከእንግዲህ ወዲህ አታዩአቸውም።


በእኔ ላይ ስለ መቈጣትህና ስለ ልብህ ትዕቢት ሁሉ ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ አሁን በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህም ልጓም አግብቼ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”


በሀገሩ ስላለ ጉዳይ በሹክሹክታ ወሬ እንዲሸበርና ወደ ሀገሩ ተመልሶ በሰይፍ እንዲገደል አደርገዋለሁ።”


“ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የሕዝብዋን ክፋት ተመልክቼአለሁ። ድምፅህንም ከፍ አድርገህ እርስዋን በመገሠጽ ተናገር።”


ዮናስም ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ተነሥቶ ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌ እጅግ ታላቅ ከተማ ከመሆንዋ የተነሣ ከተማዋን በመላ ለማዳረስ ሦስት ቀን ይፈጅ ነበር።


ነነዌ ክፉና ደጉን የማይለዩ ከአንድ መቶ ኻያ ሺህ ሕዝብ በላይ የሚኖሩባት ከተማ ነች፤ ብዙ እንስሶችም አሉባት፤ ታዲያ እኔ ለዚህች ታላቂቱ ከተማ አልራራምን?”


የናምሩድ ግዛት የነበረችውንም በሠራዊታቸው ኀይል አሦርን ድል ነሥተው ይይዛሉ፤ አሦራውያን አገራችንን ቢወሩና ድንበራችንን ቢረግጡ እርሱ ከእጃቸው ያድነናል።


ስለ ነነዌ ጥፋት ኤልቆሻዊው ናሆም የተናገረው ቃልና ያየው ራእይ የሚከተለው ነው።


እግዚአብሔር በኀይሉ በሰሜን የምትገኘውን አሦርን ያጠፋል፤ የነነዌን ከተማ ባድማ ያደርጋታል፤ እንደ ምድረ በዳም ያደርቃታል።


የነነዌ ከተማ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ዘመን ትውልድ ጋር ተነሥተው በእርሱ ላይ ይፈርዱበታል፤ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት በሰሙ ጊዜ በኃጢአታቸው ተጸጽተው ንስሓ ገብተዋልና። አሁን ግን ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።


跟着我们:

广告


广告