Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 36:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኔስ ብሆን ይህንን አገር ለመውረርና ለማጥፋት የቻልኩት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ይመስልሃልን? እንዲያውም በአገሪቱ ላይ አደጋ ጥዬ እንዳጠፋት ያዘዘኝ እግዚአብሔር ራሱ ነው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ደግሞስ ይህን ምድር ለማጥቃትና ለማጥፋት የመጣሁት ያለ እግዚአብሔር ይመስልሃልን? በዚህች አገር ላይ ዘምቼ እንዳጠፋት የነገረኝ ራሱ እግዚአብሔር ነው።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አሁንም ቢሆን፥ ጌታ፦ ወደዚህ አገር ወጥተህ አጥፋው አለኝ እንጂ፥ በውኑ ያለ ጌታ ይህን አገር ለማጥፋት የዘመትኩ ይመስልሃል?”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሁ​ንም በውኑ ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እና​ጠ​ፋ​ችሁ ዘንድ ወደ​ዚህ ሀገር ዘም​ተ​ና​ልን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ ሀገ​ራ​ቸው ዘም​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አ​ቸው” አለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አሁንም በውኑ ያለ እግዚአብሔር ይህን አገር አጠፋ ዘንድ ወጥቻለሁን? እግዚአብሔር፦ ወደዚህ አገር ወጥተህ አጥፋው አለኝ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 36:10
8 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ሽማግሌው ነቢይ የተናገረው ግን በመዋሸት ነበር።


ሌሎቹም ነቢያት ይህንኑ ቃል በመደገፍ “በራሞት ላይ ዝመት፤ ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም ድልን ይሰጥሃል” አሉት።


ስለዚህ አክዓብ አራት መቶ የሚሆኑትን ነቢያቱን ጠርቶ “ወደ ራሞት ሄጄ አደጋ ልጣልባት ወይስ ልተው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “ሄደህ አደጋ ጣልባት፤ ጌታም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲሉ መለሱለት።


እኔ በአንተ አገር ላይ አደጋ የጣልኩባትና የደመሰስኳት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ይመስልሃልን? እግዚአብሔር ራሱ በዚህች አገር ላይ አደጋ እንድጥልባትና እንድደመስሳት አዞኛል።”


ኒካዑ ግን ለኢዮስያስ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ እኔንና አንተን የሚያጣላን ምንም ነገር የለም፤ እኔ የመጣሁት ጠላቶቼን ለመውጋት እንጂ፥ አንተን ለመውጋት አይደለም፤ ጠላቶቼንም በፍጥነት እንድወጋ እግዚአብሔር አዞኛል፤ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ስለ ሆነ፥ ባትቃወመኝ ይሻልሃል፤ እምቢ ብትል ግን እግዚአብሔር ያጠፋሃል” የሚል መልእክት ላከበት፤


“እኔ ስለ አንተ ሁሉን ነገር ዐውቃለሁ፤ ምን እንደምታደርግና ወዴት እንደምትሄድ እመለከታለሁ፤ በእኔ ላይ በቊጣ መነሣሣትህንም ተረድቼአለሁ።


ለጦርነት የሚያዘጋጅ መለከት በከተማ ውስጥ ሲነፋ በፍርሃት የማይንቀጠቀጥ ሕዝብ ይኖራልን? እግዚአብሔር ካልፈቀደ በቀር በከተማ ላይ ክፉ ነገር ይመጣልን?


跟着我们:

广告


广告