Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 34:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔር እያንዳንዳቸው የት መኖር እንደሚገባቸው ወሰነ፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ለዘለዓለም ይኖሩበታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ድርሻ ድርሻቸውን ይመድብላቸዋል፤ እጁም ለክታ ታካፍላቸዋለች። ለዘላለም የእነርሱ ትሆናለች፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም ይኖሩባታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እርሱም ዕጣ ጣለባቸው፥ እጁም ለክታ ከፈለችላቸው፤ ለዘለዓለም የእነርሱ ትሆናለች፥ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ይኖሩባታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እር​ሱም ዕጣ ጣለ​ባ​ቸው፤ እጁም ከፈ​ለ​ች​ላ​ቸው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሰ​ማ​ሩ​ባ​ታል፤ ከት​ው​ል​ድም እስከ ትው​ልድ ድረስ ይወ​ር​ሱ​አ​ታል፤ በው​ስ​ጥ​ዋም ያር​ፉ​ባ​ታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እርሱም ዕጣ ጣለባቸው፥ እጁም በገመድ ከፈለችላቸው፥ ለዘላለም ይገዙአታል፥ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ይቀመጡባታል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 34:17
11 交叉引用  

ከእነርሱ በፊት አሕዛብን አባረረ፤ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ለእስራኤል ነገዶች አከፋፈለ፤ ቤቶቻቸውንም ለራሱ ሕዝብ ሰጠ።


ሕዝቦች እንደ ኀይለኛ ውሃ ድምፅ ያሰማሉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲገሥጻቸው በተራራ ላይ ገለባዎች በነፋስ እንደሚበተኑና በዐውሎ ነፋስም ዐቧራ እንደሚበተን ርቀው ይሸሻሉ።


በምሽት ጊዜ እነሆ፥ ሽብር ይሆናል፤ በማለዳ ግን ይጠፋሉ፤ የሚዘርፉንና የሚበዘብዙን ሰዎችም ዕድል ፈንታ ይኸው ነው።


ቀንና ሌሊት ትቃጠላለች፤ ጢስም ከእርስዋ መውጣቱን ለዘለዓለም አያቋርጥም፤ ምድሪቱም በዘመናት ሁሉ የማትጠቅም ባድማ ትሆናለች፤ ዳግመኛ በእርስዋ ውስጥ አልፎ የሚሄድ አይኖርም።


ጭልፊትና ጃርት ይወርሱአታል፤ የጒጒትና የቊራም መጮኺያ ትሆናለች፤ በላይዋም የመፍረስዋ መለኪያ የሆነ ገመድና የባዶነትዋ መመዘኛ የሆነ ቱምቢ ይዘረጉባታል፤


ዕድል ፈንታችሁም ይህ እንደሚሆን እግዚአብሔር ተናግሮአል። እርሱን ረስታችሁ በሐሰተኞች አማልክት ስለ ታመናችሁ በእናንተ ላይ ይህን ለማድረግ ወስኖአል።


ከዚያም በኋላ በከነዓን አገር ሰባት መንግሥታትን አጥፍቶ የእነርሱን ምድር አወረሳቸው፤


እርሱ የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም አደረገ፤ የተወሰኑ ዘመኖችንና የሚኖሩባቸውንም ቦታዎች መደበላቸው።


እስራኤል የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፤ ያዕቆብም አንጡራ ሀብቱ ነው።


ሰዎቹም የምድሪቱን ሁኔታ ለማጥናት ከመሄዳቸው በፊት ኢያሱ፥ “ወደ ምድሪቱ ሁሉ ሂዱ፤ አቀማመጥዋንም አጥንታችሁ መዝግቡ፤ ወደ እኔም ተመልሳችሁ ኑ፤ እኔም በዚህ በሴሎ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ዕጣ እጥልላችኋለሁ” የሚል መመሪያ ሰጣቸው፤


跟着我们:

广告


广告