Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 34:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ጭልፊትና ጃርት ይወርሱአታል፤ የጒጒትና የቊራም መጮኺያ ትሆናለች፤ በላይዋም የመፍረስዋ መለኪያ የሆነ ገመድና የባዶነትዋ መመዘኛ የሆነ ቱምቢ ይዘረጉባታል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ጭልፊትና ጃርት ይወርሷታል፤ ጕጕትና ቍራም ጐጆ ይሠሩባታል። እርሱ በኤዶም ላይ፣ የመፈራረሷን ገመድ፣ የመጥፊያዋንም ቱንቢ ይዘረጋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጭልፊትና ጃርት ግን ይወርሱአታል፤ ጉጉትና ቁራም ይኖሩባታል፤ በላይዋም የመፍረስ ገመድና የመጥፋት ቱንቢ ይዘረጋባታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ጭል​ፊ​ቶ​ችና ጃርት፥ ጕጕ​ትና ቍራም ይኖ​ሩ​ባ​ታል፤ መሠ​ረ​ቷ​ንም በመ​ፍ​ረስ ገመድ ይለ​ካሉ። አጋ​ን​ን​ትም ያድ​ሩ​ባ​ታል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ጭልፊትና ጃርት ግን ይወርሱአታል፥ ጕጕትና ቍራም ይኖሩባታል፥ በላይዋም የመፍረስ ገመድና የባዶነት ቱንቢ ይዘረጋባታል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 34:11
14 交叉引用  

ቀጥሎም ንጉሥ ዳዊት ሞአባውያንን ድል አደረገ፤ እስረኞቹ በመሬት ላይ እንዲጋደሙ አድርጎ ከየሦስቱ ሰዎች ሁለት ሁለቱ በሞት እንዲቀጡ አደረገ። ስለዚህም ሞአባውያን የእርሱ ተገዢዎች በመሆን ይገብሩለት ነበር።


ሰማርያንና የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ከነዘሮቹ እንደ ቀጣሁ ሁሉ ኢየሩሳሌምንም እቀጣለሁ፤ ሳሕን ከተወለወለ በኋላ ተደፍቶ እንደሚቀመጥ፥ እኔም ኢየሩሳሌምን ከኃጢአት አጸዳታለሁ።


ብቻውን በበረሓ እንደሚኖር እርኩምና በወና ቤት እንደሚኖር ጒጒት ሆኜአለሁ።


ባቢሎንን ረግረግ ስለማደርጋት የአልቅት መፈልፈያ ትሆናለች፤ ባቢሎንን ሁሉን ነገር ጠራርጎ በሚወስድ መጥረጊያ እጠርጋታለሁ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”


የፈረሰችው ከተማ ባድማ ትሆናለች፤ ማንም ሰው እንዳይገባበት ቤቱ ሁሉ ተዘግቶአል።


እግዚአብሔር እያንዳንዳቸው የት መኖር እንደሚገባቸው ወሰነ፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ለዘለዓለም ይኖሩበታል።


እግዚአብሔር የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅጽር ለማፍረስ ወስኖ ገመዱን ዘረጋ፤ ከማጥፋት አልተመለሰም፤ የመጠበቂያ ግንቡና ቅጽሩ ተፈረካከሱ፤ በአንድነትም ፈረሱ።


ሰጐን፥ ጠላቋ፥ ዝይ፥ በቋል፥ በየዐይነቱ፥


እርሱም “አሞጽ ሆይ! የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀኝ። እኔም “ቱምቢ ነው” አልኩ። ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “በቱምቢ ተስተካክሎ እንዳልተሠራ ቅጽር ሕዝቤ እስራኤል ጠማሞች ሆነው ስለ ተገኙ ይህ ቱምቢ የእስራኤልን ጠማማነት ማሳያ ምሳሌ ነው፤ ሳልቀጣቸውም አላልፍም።


የአራዊት መንጋዎች በእርስዋ ይኖራሉ፤ ልዩ ልዩ ዐይነት ጒጒቶች በጒልላትዋ ላይ ይኖራሉ፤ በየመስኮቱም ይጮኻሉ፤ በሊባኖስ ዛፍ የተሠራው ወለል ስለሚላቀቅ በመድረኩ ላይ ጥፋት ይደርሳል።


ከፍ ባለ ድምፅም እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ ሆነች! የርኩሳን መናፍስት ማደሪያ ሆነች! የሚያጸይፉና የሚያስጠሉ ወፎች መጠለያ ሆነች!


跟着我们:

广告


广告