ኢሳይያስ 33:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 እዚያም ማንም ጀልባዎችን በማይቀዝፍባቸውና ትላልቅ መርከቦች በማይንሳፈፉባቸው በወንዞችና በሰፋፊ ጅረቶች እግዚአብሔር በታላቅ ግርማው ከእኛ ጋር ይሆናል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 እግዚአብሔር በዚያ ኀይላችን ይሆናል፤ ባለመቅዘፊያ ጀልባዎች እንደማያልፉባቸው፣ ታላላቅ መርከቦችም እንደማይሻገሯቸው፣ ሰፋፊ ወንዞችና ጅረቶች ይሆንልናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ጌታ ግን በእነዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ በግርማ ከእኛ ጋር ይሆናል፤ የሚቀዘፉ መርከቦች አይገቡባትም፤ ታላላቅ መርከቦች አያልፉባትም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 የእግዚአብሔር ስም ለእናንተ ታላቅ ነው፤ ሀገራችሁም የሰፉ ወንዞችና ታላቅ የመስኖ ስፍራ ይሆናል፤ በዚህች መንገድ አትሄድም፤ መርከቦችም አይሄዱም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 እግዚአብሔር በዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ ከእኛ ጋር በግርማ ይሆናል፥ የሚቀዘፉ መርከቦች አይገቡባትም፥ ታላላቆችም መርከቦች አያልፉባትም። 参见章节 |