Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 33:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እናንተ ለኖራ እንደሚቃጠሉና ለእሳት እንደሚቈረጥ እሾኽ ትሆናላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሕዝቦች ኖራ እንደሚወጣው ድንጋይ ይቃጠላሉ፤ እንደ እሾኽ ቍጥቋጦ በእሳት ይጋያሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፥ ተቆርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አሕ​ዛ​ብም በእ​ርሻ ውስጥ ተቈ​ርጦ እንደ ተጣ​ለና በእ​ሳት እንደ ተቃ​ጠለ እሾህ የተ​ቃ​ጠሉ ይሆ​ናሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፥ ተቆርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 33:12
8 交叉引用  

ዙሪያዬን እንደ ንብ ከበቡኝ፤ ነገር ግን እሾኽ በእሳት እንደሚቃጠል በፍጥነት ተቃጠሉ፤ በእግዚአብሔርም ኀይል ደመሰስኳቸው።


የእስራኤል ብርሃን እግዚአብሔር ራሱ እሳት ይሆንባቸዋል፤ የእስራኤልም ቅዱስ አምላክ ራሱ በአንዲት ቀን ኲርንችቱንና እሾኹን ሳያስቀር ሁሉን በልቶ እንደሚጨርስ የእሳት ነበልባል ይሆናል።


ዳግመኛ በወይን ቦታዬ ላይ አልቈጣም፤ የወይን ቦታዬን የሚያበላሹ ኲርንችትና እሾኽ ቢኖሩ ነቃቅዬ በእሳት በማቃጠል ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ።


በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ።


ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ወጣቶቻቸውን ይቀጣል፤ ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶችና አሳዳጊ ለሌላቸው ለሙት ልጆቻቸው አይራራም፤ ሁሉም እያንዳንዱ ከሐዲና ክፉ አድራጊ ሆኖአል፤ ከእያንዳንዱም ሰው አንደበት የሚነገረው ቃል ተንኰል የሞላበት ነው፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ ገና አልበረደም፤ ስለዚህ እነርሱን ለመቅጣት እጁ እንደ ተቃጣ ነው።


የሕዝቡ ክፋት ኲርንችቱንና እሾኹን እንደሚያቃጥል እሳት ነው፤ እንደ በረሓ እሳት ደኑን በሚያቃጥልበት ጊዜ ጢሱ ተትጐልጒሎ ሲወጣ ቀጥ ብሎ የቆመ ዐምድ ይመስላል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የሞአብ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ የኤዶምን ንጉሥ ዐፅም ዐመድ እስኪሆን አቃጥለዋል፤


跟着我们:

广告


广告