ኢሳይያስ 32:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ቤተ መንግሥቱ ሳይቀር ወና ይሆናል፤ መናገሻ ከተማውም የተፈታ ምድረ በዳ ይሆናል፤ ቤቶችና የመጠበቂያ ማማዎች ይፈርሳሉ፤ የሜዳ አህዮች መራገጫና የመንጋ መሰማርያ ይሆናሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ዐምባ ምሽጉ ወና ይሆናል፤ ውካታ የበዛበት ከተማ ጭር ይላል፤ ምሽጉና ማማው ለዘላለሙ ዋሻ፣ የዱር አህያ መፈንጫ፣ የመንጋም መሰማሪያ ይሆናል፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 አዳራሹ ወና ይሆናል፥ በሰው የተጨናነቀውም ከተማ ወና ይሆናል፤ ምሽጉና ግንቡም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 የበለጸገች ከተማና ቤቶችዋ ምድረ በዳ ይሆናሉ። የከተማውን ሀብትና ያማሩ ቤቶችን ይተዋሉ፤ አንባዎችም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማሪያ ይሆናሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 አዳራሹ ወና ትሆናለችና፥ የብዙ ሰውም ከተማ ትለቀቃለችና፥ አምባውና ግንቡም ለዘላለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናልና። 参见章节 |