Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 30:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ነገር ግን የግብጽ ንጉሥ ጥበቃ ወደ ኀፍረት፥ የግብጽም ከለላ ወደ ውርደት ያደርሳቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ነገር ግን የፈርዖን ከለላ ውርደት ይሆንባችኋል፤ የግብጽም ጥላ ኀፍረት ያመጣባችኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለዚህ የፈርዖን ኃይል እፍረት፥ በግብጽም ጥላ መታመን ስድብ ይሆንባቸዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ስለ​ዚህ የፈ​ር​ዖን ኀይል እፍ​ረት፥ በግ​ብፅ መታ​መ​ንም ስድብ ይሆ​ን​ባ​ች​ኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ስለዚህ የፈርዖን ኃይል እፍረት በግብጽም ጥላ መታመን ስድብ ይሆንባችኋል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 30:3
18 交叉引用  

የግብጽ ንጉሥ ይረዳኛል ብለህ አስበህ ከሆነ፥ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ እንደሚመረኰዝ ሰው መሆንህ ነው፤ እርሱ ተሰብሮ ስንጣሪው እጅህን ያቈስልሃል፤ እንግዲህ የግብጽ ንጉሥ ለሚተማመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው’ ሲል የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይጠይቅሃል።”


የሰው ርዳታ ከንቱ ነው፤ ስለዚህ ጠላቶቻችንን ድል እንድናደርግ አንተ እርዳን።


በመከራ ጊዜ በማይታመን ሰው ላይ መደገፍ በተነቃነቀ ጥርስ እንደማኘክና በተሰበረ እግር እንደ መራመድ ያኽል ነው።


በኢትዮጵያ የሚተማመኑና በግብጽም የሚመኩ ሁሉ ግራ ተጋብተው ተስፋ ይቈርጣሉ።


በዚያን ጊዜ በባሕር ዳርቻ የሚኖሩ ሰዎች፦ ‘እኛን ከአሦር ንጉሠ ነገሥት ያድኑናል ብለን ተስፋ ያደረግንባቸውና ወደ እነርሱ የተጠጋንባቸው አገሮች ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ! እኛማ እንዴት እናመልጣለን?’ ” ይላሉ።


ምንአልባት ግብጽ ትረዳኛለች ብለህ ተስፋ አድርገህ ይሆናል፤ ነገር ግን በእርስዋ መታመን በሸምበቆ የመደገፍ ያኽል መሆኑን ዕወቀው፤ ተሰንጥሮ እጅህን ከሚወጋው በቀር ሸምበቆ ለምንም አይጠቅምህም፤ በግብጽ ንጉሥ የሚተማመንም የሚገጥመው ዕድል ይህንኑ የመሰለ ነው።’ ”


ወደ ባዕዳን ሕዝብ አማልክት ዘወር በማለትሽ ራስሽን አቃለሻል፤ ከዚህ በፊት በአሦር ምክንያት ኀፍረት እንደ ደረሰብሽ አሁን ደግሞ በግብጽ ምክንያት ኀፍረት ይደርስብሻል።


“የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ ግብጽ እንሄዳለን ብላችሁ ብትወስኑ ከዚህ በፊት በኢየሩሳሌም ሕዝብ ላይ የወረደው ቊጣዬና መዓቴ በእናንተም ላይ ይወርዳል፤ ለሕዝብ ሁሉ አስፈሪ መቀጣጫ ትሆናላችሁ፤ የሚያዩአችሁም ሕዝብ ሁሉ መዘባበቻ ያደርጓችኋል፤ ስማችሁም ለመሳለቂያ ይሆናል፤ ይህችንም ስፍራ ዳግመኛ አታዩአትም።’ ”


ስለዚህ አሁን ሄዳችሁ ልትኖሩ በምትፈልጉበት ቦታ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንደምትሞቱ እርግጠኞች ሁኑ።”


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ግብጽን፥ አማልክትዋንና ነገሥታቶችዋን፥ የቴብስ አምላክ የሆነውን አሞንን፥ የግብጽን ንጉሥና በእርሱ የሚተማመኑትን ሁሉ እቀጣለሁ።


በእጆቻችሁ በያዙአችሁ ጊዜ ተሰነጣጥቃችሁ ትከሻቸውን ወጋችሁ፤ በእናንተ ላይ በተደገፉ ጊዜ እናንተ ተሰብራችሁ ወገባቸው ተብረከረከ።


ጣዖቱ ወደ አሦር በመወሰድ ለታላቁ ንጉሥ እጅ መንሻ ሆኖ ይቀርባል፤ እስራኤል ከተከተለው ክፉ ምክር የተነሣ ኀፍረትና ውርደት ይደርስበታል።


በቅዱስ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው፦ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም።”


በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ሞላ ተስፋው አያሳፍርም።


跟着我们:

广告


广告