Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 25:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የታላላቅ መንግሥታት ሕዝቦች ያከብሩሃል፤ በጨካኞች መንግሥታት ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ይፈሩሃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህ ብርቱ ሕዝቦች ያከብሩሃል፤ የጨካኝ አሕዛብ ከተሞችም ይፈሩሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለዚህ ኃያላኑ ወገኖች ያከብሩሃል፥ የጨካኞች አሕዛብ ከተማም ትፈራሃለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ስለ​ዚህ ድሆች ወገ​ኖች ያከ​ብ​ሩ​ሃል፤ የተ​ገፉ ሰዎች ከተ​ሞ​ችም ያከ​ብ​ሩ​ሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ስለዚህ ኃያላኑ ወገኖች ያከብሩሃል፥ የጨካኞች አሕዛብ ከተማም ትፈራሃለች።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 25:3
16 交叉引用  

እንዲህም በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ድንቅ ነው! ኀይልህ እጅግ ታላቅ በመሆኑ ጠላቶችህ በፍርሃት በፊትህ ይሸማቀቃሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዓለምን ስለ ክፋቱ፥ ክፉዎችን ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፤ የኲራተኞችን ማን አለብኝነት አዋርዳለሁ፤ የትዕቢተኛውንም ጭካኔ አጠፋለሁ።


ስለዚህ በምሥራቅ ያሉት ለእግዚአብሔር ክብር ይሰጣሉ፤ በደሴቶች ያሉ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።


ኢየሩሳሌም ሆይ! በአንቺ ላይ በጠላትነት የሚነሡ የጠላት ሠራዊት ሁሉ እንደ ትቢያ በነው ይጠፋሉ፤ እጅግ የሚያስፈሩ ሠራዊቶቻቸውም ሳይታሰቡ በድንገት በነፋስ እንደሚወሰድ ገለባ ይሆናሉ።


በዚህም ዐይነት ታላቅነቴንና ቅድስናዬን አሳያለሁ፤ በብዙ ሕዝቦችም ዘንድ ራሴን አሳውቃለሁ፤ ከዚያ በኋላ እነርሱ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”


እንደ እባብና እንደ ሌሎችም ተንፏቃቂ ፍጥረቶች ትቢያ ይልሳሉ፤ ከምሽጎቻቸው ወጥተው እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ፤ በፍርሃትም ወደ አንተ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ አንተንም እየፈሩ ይኖራሉ።


ከዚያም በኋላ ኢየሩሳሌምን ከወጉአት መንግሥታት መካከል ከጥፋት የተረፉት ለንጉሡ ለሠራዊት አምላክ ሊሰግዱለትና የዳስ በዓልንም ለማክበር በየዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣሉ።


በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ይነግሣል፤ ሰዎችም አምላክ እርሱ ብቻ መሆኑን ያምናሉ፤ የእርሱንም ስም ብቻ ይጠራሉ።


በዚያኑ ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የከተማይቱም አንድ ዐሥረኛ ፈራረሰ፤ በምድር መናወጥም ምክንያት ሰባት ሺህ ሰዎች ሞቱ፤ ከሞት የተረፉትም እጅግ ፈሩ፤ የሰማይንም አምላክ አከበሩ።


跟着我们:

广告


广告