Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 21:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ባየሁትም ራእይ ግብዣ ተዘጋጅቶ ለእንግዶች መቀመጫ ስጋጃዎች ተነጥፈዋል፤ እነርሱም ገና በመብላትና በመጠጣት ላይ ሳሉ፥ “እናንተ የጦር መኰንኖች! ጋሻችሁን ወልውላችሁ አዘጋጁ!” የሚል ድንገተኛ ትእዛዝ ተላለፈላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ማእዱን አሰናዱ፤ ምንጣፉን አነጠፉ፤ በሉ፤ ጠጡ! እናንተ ሹማምት ተነሡ፤ ጋሻውን በዘይት ወልውሉ!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ማዕዱን ያዘጋጃሉ፥ ምንጣፉንም ይዘረጋሉ፥ ይበላሉም፥ ይጠጣሉም፤ እናንተ መሳፍንት ሆይ፥ ተነሡ፥ ጋሻውን አዘጋጁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ማዕ​ዱን አዘ​ጋጁ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እና​ንተ አለ​ቆች ሆይ፥ ተነሡ፤ ጋሻ​ው​ንም አዘ​ጋጁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ማዕዱን ያዘጋጃሉ፥ ምንጣፉንም ይዘረጋሉ፥ ይበሉማል፥ ይጠጡማል፥ እናንተ መሳፍንት ሆይ፥ ተነሡ፥ ጋሻውን አዘጋጁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 21:5
12 交叉引用  

“እናንተ የጊልቦዓ ተራራዎች ሆይ! ዝንብም ሆነ ጤዛ አይውረድባችሁ! የእርሻ መሬቶቻችሁም ምንም ነገር አይብቀልባቸው! የጀግኖች ጋሻዎች እዚያ በውርደት ወድቀዋልና፤ የሳኦልም ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና።


ምንም ነገር በማይበቅልበት ተራራ ጫፍ ሆናችሁ ምልክት ስጡ፤ ወደ ትዕቢተኞቹ የባቢሎን ገዢዎች ወደሚያስገባው በር እንዲገቡ ትእዛዝ ስጡ።


“ጋሻችሁን አዘጋጁ፤ ወደ ጦር ሜዳም ዝመቱ፤


የእግዚአብሔር ዓላማ ስለ ቤተ መቅደሱ የበቀል ዕርምጃ ለመውሰድ ስለ ሆነ ባቢሎንን ለማጥፋት የሜዶንን ነገሥታት አነሣሥቶአል፤ ስለዚህ ፍላጻችሁን ሳሉ! ጋሻችሁንም አንሡ!


ሞቅ ባላቸው ጊዜ የመጠጥ ግብዣ አደርግላቸዋለሁ፤ እስኪሰክሩ ድረስም አጠጣቸዋለሁ፤ ከዚያም ዘለዓለማዊ እንቅልፍ ያንቀላፋሉ፤ እስከ መቼም አይነቁም።


መሳፍንትዋ፥ የጥበብ ሰዎችዋ፥ መሪዎችዋ፥ የጦር አዛዦችዋና ወታደሮችዋ ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይተኛሉ፤ እስከ ዘለዓለም አይነቁም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ንጉሡ ነኝ፤ ስሜም የሠራዊት አምላክ ነው።


እንደ ሰው አስተሳሰብ እኔ በኤፌሶን ከአራዊት ጋር መታገሌ ጥቅሜ ምንድን ነው? ሙታን ከሞት የማይነሡ ከሆነማ “ነገ ስለምንሞት ኑ እንብላ፤ እንጠጣ” እንደ ተባለው መሆኑ ነው።


跟着我们:

广告


广告