Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 21:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለ ዐረብ አገር የተነገረውም ቃል ይህ ነው፤ ከጭነት ግመሎቻችሁ ጋር በዐረብ በረሓ የምትሰፍሩ እናንተ የደዳን ሕዝብ ሆይ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለ ዐረብ አገር የተነገረ ንግር፤ እናንተ በዐረብ ዱር የምትሰፍሩ፣ የድዳን ሲራራ ነጋዴዎች፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ስለ አረብ የተነገረ ሸክም። የድዳናውያን ነጋዴዎች ሆይ፥ በዓረብ ዱር ወስጥ ታድራላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሌሊ​ትም በዲ​ዳ​ና​ው​ያን ጎዳና በዛ​ፎች ውስጥ ታድ​ራ​ለህ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስለ ዓረብ የተነገረ ሸክም። የድዳናውያን ነጋዴዎች ሆይ፥ በዓረብ ዱር ወስጥ ታድራላችሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 21:13
14 交叉引用  

የኩሽ ልጆች፦ ሳባ፥ ሐዊላ፥ ሳብታ፥ ራዕማና ሳብተካ ናቸው። የራማ ልጆች፥ ሳባና ደዳን ናቸው።


ዮቅሻንም ሳባንና ደዳንን ወለደ፤ የደዳንም ዘሮች አሹራውያን፥ ሌጡሻውያንና ሌኡማውያን ናቸው።


ይህም ሁሉ ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር።


አብርሃም ቀጡራ ተብላ ከምትጠራው ቊባቱ ዚምራን፥ ዮቅሻን፥ መዳን፥ ምድያም፥ ዩሽባቅና ሹሐ ተብለው የሚጠሩትን ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዮቅሻንም ሳባና ደዳን ተብለው የሚጠሩትን ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፤


የኩሽ ልጆች ሳባ፥ ሐዊላ፥ ሰብታ፥ ራዕማና ሳብተካ ናቸው፤ የራዕማ ወንዶች ልጆች ሳባና ድዳን ናቸው።


የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ እግዚአብሔር ገልጦለት ስለ ባቢሎን የተናገረው የትንቢት ቃል ይህ ነው፤


ዳግመኛ የሚኖርባትም አይገኝም፤ የበረሓ ዘላኖች የሆኑ ዐረቦችም ድንኳን አይተክሉባትም፤ እረኞችም መንጋ አያሰማሩባትም።


ዘብ ጠባቂውም “በእርግጥ የሌሊቱ ንጋት እየተቃረበ ነው፤ ነገር ግን ሌሊቱ ተመልሶ ይመጣል፤ እንደገና ጠይቀህ ለመረዳት ብትፈልግ ተመልሰህ ናና ጠይቅ” አለው።


የዔሳውን ዘር በምቀጣበት ጊዜ መከራን ስለማመጣባቸው፥ የደዳን ከተማ ሕዝብ ሆይ! ወደ ኋላ ተመልሳችሁ ሩጡ! በዋሻም ተሸሸጉ!


ከሮድ አገር ሰዎች ጋር የንግድ ሥራ ታካሂጂ ነበር፤ በባሕር ዳር የሚገኙ አገሮች ሕዝቦች ሸቀጥሽን ወስደው በምትኩ የዝሆን ጥርስና ዞጲ ያመጡልሽ ነበር።


አጋር በዐረብ አገር ለሚገኘው ለሲና ተራራ ምሳሌ ነበረች፤ ስለዚህ ከአሁኒቱ ኢየሩሳሌም ጋር ትመሳሰላለች፤ እርስዋ ከነልጆችዋ በባርነት የምትገኝ ናት።


跟着我们:

广告


广告