Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 2:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እንግዲህ ትንፋሹ አፍንጫው ላይ በሆነች በሟች ሰው መተማመናችሁ ይቅር፤ እርሱ ለምንም አይጠቅምም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እስትንፋስ አፍንጫው ላይ ባለች በሰው አትታመኑ፤ ከቶ ምን የሚበጅ ነገር አለው!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እስትንፋስ አፍንጫው ላይ ባለች በሰው አትታመኑ፤ ከቶ ምን የሚበጅ ነገር አለው!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እስ​ት​ን​ፋሱ በአ​ፍ​ን​ጫው ያለ​በ​ትን ሰው ተዉት፤ እርሱ ስለ ምን ይቈ​ጠ​ራል?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እስትንፋሱ በአፍንጫው ውስጥ ያለበትን ሰው ተዉት፥ እርሱ ስለ ምን ይቆጠራል?

参见章节 复制




ኢሳይያስ 2:22
14 交叉引用  

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።


በምድር ላይ የሚኖር እስትንፋስ ያለው ነገር ሁሉ ሞተ።


እግዚአብሔር የሕይወት እስትንፋስ ሰጥቶኝ እስከ አለሁ ድረስ


ማዳን ስለማይችሉ በመሪዎች ወይም በማንኛውም ፍጡር አትተማመኑ።


ተራ ሰዎች እንደ አየር ናቸው፤ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ተጨባጭነት እንደሌለው ምኞት ናቸው፤ ሁለቱ በሚዛን ላይ ቢቀመጡ ከነፋስ ሽውታ ይቀላሉ።


አንተ እርሱን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? እርሱንስ ትጐበኘው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?


በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቦች እንደ አንድ የውሃ ጠብታ ናቸው፤ በሚዛንም ላይ እንዳለ ዐቧራ ናቸው፤ ደሴቶችም በእርሱ ዘንድ እንደ ትቢያ የቀለሉ ናቸው።


በእግዚአብሔር ዘንድ ሕዝቦች ሁሉ እንዳሉ የሚቈጠሩ አይደሉም። እነርሱ በእርሱ ዘንድ እንደ ኢምንት የሚቈጠሩና ዋጋ የሌላቸው ናቸው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የማጽናናችሁ እኔ ራሴ ነኝ፤ ታዲያ እንደ ሣር የሚጠወልገውንና መሞት ያለበትን ሰውን የምትፈሩት ለምንድን ነው?


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔን ትቶ በሰው የሚታመንና፥ ‘ኀይል ይሆነኛል’ ብሎ በሥጋ ለባሽ ሰው የሚመካ የተረገመ ይሁን።


እንደምናየው ከሆነ እነሆ፥ ክፉ አድራጊዎች ዕድለኞች ናቸው፤ በእርግጥም እነርሱ በብልጽግና ይኖራሉ፤ እግዚአብሔርን እንኳ እየተፈታተኑት ምንም ችግር አይደርስባቸውም እያላችሁ ትናገራላችሁ።’ ”


ነገ የሚሆነውን አታውቁም፤ ሕይወታችሁ ምንድን ነው? ለአንድ አፍታ ታይቶ በኋላ እንደሚጠፋ ጉም ናችሁ።


跟着我们:

广告


广告