Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 19:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 መንጠቆአቸውን ወደ አባይ ወንዝ የሚጥሉ ዓሣ አጥማጆች ያዝናሉ፤ ያለቅሳሉም፤ መረቦቻቸውንም በውሃ ላይ የሚዘረጉ ተስፋ ይቈርጣሉ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ዓሣ አጥማጆች ያዝናሉ፤ በአባይ ወንዝ ላይ መንጠቋቸውን የሚወረውሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤ በውሃ ላይ መረባቸውን የሚጥሉ ሁሉ፣ ጕልበታቸው ይዝላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፤ በዐባይ ወንዝ ላይ መንጠቆአቸውን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት በድካም ይዝላሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዓሣ አጥ​ማ​ጆቹ ያዝ​ናሉ፤ በዓ​ባ​ይም ወንዝ መቃ​ጥን የሚ​ጥ​ሉት ሁሉ ያለ​ቅ​ሳሉ፤ በው​ኆ​ችም ላይ መረብ የሚ​ዘ​ረ​ጉት ያለ​ቅ​ሳሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 19:8
6 交叉引用  

በወንዝ ውስጥ ያሉት ዓሣዎች ሁሉ ሞቱ፤ የዐባይ ወንዝ ውሃ ስለ ገማ ግብጻውያን ሊጠጡት አልቻሉም። በግብጽ ምድር ደም የሌለበት ስፍራ አልነበረም።


ከዔንገዲ ጀምሮ እስከ ዔንዔግላይም ድረስ ዓሣ አጥማጆች ይቆማሉ፤ ያም ቦታ መረቦች የሚዘረጉበት ቦታ ይሆናል፤ በሜዲትራኒያን ባሕር እንደሚገኘው ዐይነት በዚህም ልዩ ልዩ ዓሣ ይገኛል።


ዓሣ በመንጠቆ እንደሚያዝ ጠላት ሁሉንም ይይዛቸዋል፤ በመረብም እንደሚጐተት ይጐትታቸዋል፤ በማከማቻው ይሰበስባቸዋል፤ ይህን በማድረጉ በደስታ ይፈነጥዛል።


ታዲያ እርሱ መረቡን እያራገፈና ያለምሕረት ሕዝቦችን እየፈጀ መቀጠል አለበትን?


በግብጽ ሳለን ምንም ዋጋ ሳንከፍል የፈለግነውን ያኽል ዓሣ እንበላ እንደ ነበረ እናስታውሳለን፤ በዚያ ሳለን እንበላ የነበረውን ዱባ፥ (ኪያር) ሀብሀብ (በጢኽ)፥ ኲራት (ድንች መሳይ ምግብ) ቀዩንና ነጩን ሽንኩርት፥


‘ዋሽንት ነፋንላችሁ አልጨፈራችሁም! ሙሾ አወረድንላችሁ አላለቀሳችሁም!’ የሚሉትን ልጆች ይመስላሉ።


跟着我们:

广告


广告