Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 14:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በመጨረሻ ግን እነሆ ዓለም ሁሉ የሰላም ዕረፍት ያገኛል፤ ሁሉም በደስታ ይዘምራሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ምድር ሁሉ ሰላምና ዕረፍት አግኝታለች፤ የደስታም ዝማሬ ታስተጋባለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ምድርም ሁሉ አርፋ በጸጥታ ተቀምጣለች እልልም ብላለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ምድ​ርም ሁሉ ዐርፋ በጸ​ጥታ ተቀ​ም​ጣ​ለች፤ እል​ልም ብላ​ለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ምድርም ሁሉ አርፋ በጸጥታ ተቀምጣለች እልልም ብላለች።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 14:7
13 交叉引用  

ሕዝቦች ሁሉ፥ በደስታ አጨብጭቡ! ከፍ ባለ ድምፅ በመዘመር፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ!


ድንቅ ነገሮችን ስላደረገና፥ በኀያል ሥልጣኑ ድልን ስለ ተጐናጸፈ፥ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩለት!


ለጻድቃን፥ ሁሉ ነገር ሲሳካላቸው በከተማው ውስጥ ደስታ ይሆናል። ክፉዎች ሲጠፉ ደግሞ እልልታ ይሆናል።


አስፈሪ የሆነ ራእይ ተገልጦልኛል፤ ይኸውም አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ ከዳተኛው ይከዳል፤ ዘራፊውም ይዘርፋል። የዔላም ሠራዊት ሆይ! አደጋ ለመጣል ውጡ! የሜዶን ሠራዊት ሆይ! ከተሞችን ክበቡ! እግዚአብሔር በባቢሎን ምክንያት የደረሰውን ሥቃይ ሁሉ ያስወግዳል።


እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚያጽናና እና ለሚሠቃዩትም ስለሚራራ ሰማያት ሆይ! ዘምሩ፤ ምድር ሆይ! ደስ ይበልሽ፤ ተራራዎች ሆይ! እልል በሉ።


ባቢሎን ከሰሜን በሚመጡ አጥፊዎች እጅ በወደቀች ጊዜ በሰማይና በምድር የሚገኝ ሠራዊት ሁሉ በደስታ እልል ይላል።


ስለዚህም እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፦ “ዓለም ሁሉ ሲደሰት የእናንተን አገር ግን ባድማ አደርጋታለሁ።


እነርሱም “ምድርን ሁሉ ዞረን መረመርን፤ ምድሪቱ በመላ ሰላም ነች” ብለው ለመልአኩ ነገሩት።


ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!


跟着我们:

广告


广告