Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 10:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የዓለም መንግሥታት ሁሉ በእኔ ፊት እንደ ወፍ ጎጆች ነበሩ፤ እንቊላል በቀላሉ እንደሚሰበሰብ ዐይነት ሀብታቸውን ሁሉ ሰብስቤ ወሰድኩ፤ ይህን ባደረግሁ ጊዜ የወፍ ላባ ያኽል እንኳ የተንቀሳቀሰ የለም፤ የወፍ ኩምቢ ያኽል እንኳ ድምፁን ያሰማ የለም።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሰው እጁን ወደ ወፍ ጐጆ እንደሚሰድድ፣ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቍላል እንደሚሰበስቡ፣ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሰው እጁን ወደ ወፍ ጎጆ እንደሚሰድ፤ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቁላል እንደሚሰበስቡ፤ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ከተ​ሞች አና​ው​ጣ​ለሁ። በእ​ጄም ዓለ​ምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ እንደ ተተወ እን​ቍ​ላ​ልም እወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ኔም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ የሚ​ቃ​ወ​መ​ኝም የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እጄም የአሕዛብን ኃይል እንደ ወፍ ቤት አገኘች፥ የተተወም እንቍላል እንደሚሰበሰብ እንዲሁ እኔ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፥ ክንፉን የሚያራግብ አፉንም የሚከፍት የሚጮኽም የለም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 10:14
14 交叉引用  

የቀድሞ አባቶቼና እኔ በሌሎች ሕዝቦች ላይ ምን እንዳደረግን አታውቁምን? ከሌሎች ሕዝቦች አማልእክት መካከል ሕዝቡን ከአሦር ንጉሠ ነገሥት ያዳነ አምላክ አንድ እንኳ ይገኛልን?


‘ሀብቴ በዝቷል፥ በብልጽግናዬም ብዙ ገንዘብ አግኝቼአለሁ’ ብዬ ተደስቼ አላውቅም።


ትዕቢት ጥፋትን ያመጣል፤ ትሕትና ግን ክብርን ያጐናጽፋል። ክብርን ግን ትሕትና ይቀድመዋል።


እነዚህ ገዢዎች በቊጣቸው ሕዝቦችን ሲጨቊኑ ኖረዋል፤ ያሸነፉአቸውንም ያለማቋረጥ ሲያሠቃዩአቸው ነበር፤


በባዕዳን አገሮች ጒድጓዶችን ቆፍሬ ውሃ ጠጥቻለሁ፤ የብዙ ሠራዊቴ እግር የግብጽን ወንዞች አድርቋል’ ብለህ ተመክተሃል።


በአገሪቱ ላይ መኖር የሚገባችሁ እናንተ ብቻ መስሎአችሁ፥ ቀድሞ በነበራችሁ ይዞታ ላይ ለመቀላቀል ሰዎችን ሁሉ እያስወጣችሁ ቤትን ከቤት ማያያዝና እርሻንም በእርሻ ላይ ለመቀላቀል ለምትፈልጉ ወዮላችሁ!


አለታማው ገደል ላይ የምትኖሪ፥ እስከ ተራራማው ጫፍ ድረስ የምትደርሽ ሆይ! ተፈሪነትሽና የልብሽ ኲራት አታለውሻል፤ ምንም እንኳ መኖሪያሽን እንደ ንስር ጎጆ ብታደርጊ እኔ ከዚያ ላይ አወርድሻለሁ ይላል እግዚአብሔር።”


በእኔ ላይ መገዳደራችሁንና ያለ ገደብም በእኔ ላይ መናገራችሁን ሰምቼአለሁ።”


ነገር ግን እንደ ንስር ወደ ላይ ብትበር፥ መኖሪያህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ። ይህን እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።”


የከተማይቱ ሀብት መጨረሻ የለውም፤ የከበሩ ድንጋዮቹም የተትረፈረፉ ናቸው፤ ስለዚህ ሄዳችሁ ብሩንና ወርቁን በዝብዛችሁ ውሰዱ።


跟着我们:

广告


广告