ኢሳይያስ 1:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 ገለባ በእሳት ብልጭታ እንደሚጋይ “ኀይለኞች ነን” የሚሉ ሰዎች ይጠፋሉ፤ እንደ ቃጠሎ እሳት በእነርሱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት የሚያቆም የለም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም31 ብርቱ ሰው እንደ ገለባ፣ ሥራውም እንደ ብልጭታ ይሆናል፤ ሁለቱም ዐብረው ይቃጠላሉ፤ እሳቱንም የሚያጠፋው የለም።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 ብርቱ ሰው እንደ ገለባ፤ ሥራውም እንደ ብልጭታ ይሆናል፤ ሁለቱም አብረው ይቃጠላሉ፤ እሳቱንም የሚያጠፋው የለም።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 ኀይላቸውም እንደ መቃ መስዬ፥ ሥራቸውም እንደ ጠለሸት ይሆናል፤ ኃጥአንና ዐማፅያንም አብረው ይቃጠላሉ፤ እሳቱንም የሚያጠፋላቸው ያጣሉ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 ኃይለኛውም እንደ ተልባ ጭረት፥ ሥራውም እንደ ጠለሸት ይሆናል፥ አብረውም ይቃጠላሉ እነርሱንም የሚያጠፋ የለም። 参见章节 |