ሆሴዕ 7:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 “ሁሉም በቊጣ እንደ ምድጃ ግለው ገዢዎቻቸውን ፈጁ፤ ንጉሦቻቸውንም በየተራ አጠፉ፤ ይህም ሁሉ ሲሆን ከእነርሱ አንድ እንኳ የእኔን ርዳታ የጠየቀ የለም።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ ገዦቻቸውን ፈጁ፤ ንጉሦቻቸው ሁሉ ወደቁ፤ ከእነርሱም ወደ እኔ የቀረበ ማንም የለም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ሁሉም እንደ ምድጃ ግለዋል፥ ፈራጆቻቸውንም አጥፍተዋል፤ ነገሥታቶቻቸውም ሁሉ ወድቀዋል፤ ከእነርሱም መካከል ወደ እኔ የጮኸ የለም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ሁሉም እንደ ምድጃ ግለዋል፤ ፈራጆቻቸውንም በሉ፤ ነገሥታቶቻቸውም ሁሉ ወደቁ፤ ከእነርሱም መካከል የሚጠራኝ የለም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ሁሉም እንደ ምድጃ ግለዋል፥ ፈራጆቻቸውንም በሉ፥ ነገሥታቶቻቸውም ሁሉ ወደቁ፥ ከእነርሱም ወደ እኔ የሚጮኽ የለም። 参见章节 |