Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 6:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እጅግ የሚያሠቅቅ ነገር በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ አይቼአለሁ፤ ይኸውም ሕዝቡ ጣዖትን በማምለክ ዝሙት ረክሶአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ ኤፍሬም ዘማዊ ሆነ፤ እስራኤልም ረከሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በእስራኤል ቤት የሚያስፈራን ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ የኤፍሬም ዝሙት አለ፥ እስራኤልም ረክሶአል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት የሚ​ያ​ሰ​ፈ​ራን ነገር አይ​ቻ​ለሁ፤ በዚያ የኤ​ፍ​ሬ​ም​ንም ዝሙት አየሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ረክ​ሶ​አል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በእስራኤል ቤት የሚያስፈራን ነገር አይቻለሁ፥ በዚያ በኤፍሬም ውስጥ ግልሙትና ተገኘ፥ እስራኤልም ረክሶአል።

参见章节 复制




ሆሴዕ 6:10
14 交叉引用  

ሮብዓም ግን የሽማግሌዎቹን ምክር ቸል በማለት አብሮ ዐደጎቹ ወደነበሩት፥ አሁን ደግሞ አማካሪዎቹ ወደሆኑት ወጣቶች ዘንድ ሄዶ፤


ይህም የሆነበት ምክንያት ኢዮርብዓም ራሱ በሠራው ኃጢአትና የእስራኤልም ሕዝብ ኃጢአት እንዲሠሩ በማድረግ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቊጣ ስላነሣሣ ነው።


ይህም የሆነበት ምክንያት እስራኤላውያን በሠሩት ኃጢአት ከግብጽ ንጉሥ እጅ በመታደግ አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር የመራቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን በማሳዘናቸው ነበር፤ ይኸውም ለባዕዳን አማልክት ሰገዱ፤


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን የመሰለ ነገር በሕዝቦች መካከል ተሰምቶ እንደ ሆነ ጠይቁ፤ የተለዩ የእስራኤል ሕዝብ በጣም አጸያፊ የሆነ ነገር አድርገዋል።


ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚገኙ ነቢያትም ከዚህ የባሰ ክፋት ሲያደርጉ አይቼአለሁ፤ እነርሱ ያመነዝራሉ፤ ሐሰትም ይናገራሉ፤ ሰዎችን ለክፉ ሥራ ያነሣሣሉ፤ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ ከክፉ ሥራቸው አይመለሱም። ስለዚህ እነርሱ በእኔ ዘንድ እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ሕዝብ የከፉ ናቸው።


ኢዮስያስ በነገሠበት ዘመን እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “እምነት አጒዳይ የሆነችው እስራኤል ምን እንዳደረገች አይተሃልን? እርስዋ ከእኔ ተለይታ በየከፍተኛው ተራራና በየለመለመው ዛፍ ሥር ጣዖትን በማምለክ ርኲሰትን ፈጽማለች።


ኦሆላ እኔ ካገባኋት በኋላ እንኳ አመንዝራነትዋን ቀጠለች፤ በአሦራውያን ወዳጆችዋም ፍቅር ተቃጠለች።


እርስዋም ለአሦራውያን ባለ ሥልጣኖች ሁሉ መጠቀሚያ አመንዝራ ነበረች፤ ፍትወትዋም የአሦራውያንን ጣዖቶች በማምለክ ራስዋን እንድታረክስ አደረጋት።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የዝሙት ሥራ፥ የቈየና አዲስ የወይን ጠጅን መከተል የሕዝቤን አእምሮ አጥፍቶአል።


ስለዚህ ከእንጨት የተሠራውን ጣዖት ምክር ይጠይቁታል፤ የጥንቈላ ዘንጋቸውም ለጥያቄአቸው መልስ የሚሰጥ ይመስላቸዋል፤ በዝሙት መንፈስም ተመርተው ከእግዚአብሔር ርቀዋል።


የእስራኤል ሕዝብ ከጣዖት አምልኮ ጋር ስለ ተጣመሩ ተዉአቸው የፈለጉትን ያድርጉ።


“እኔ የአንቺን የእስራኤልን ሁኔታ ዐውቃለሁ፤ ከእኔ መሰወር አይቻልሽም፤ በጣዖት አምልኮ ዝሙት ረክሰሻል።”


跟着我们:

广告


广告