ሆሴዕ 12:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ የያዕቆብንም ልጆች እንደ አካሄዳቸው ይቀጣቸዋል፤ ባደረጉትም ክፉ ሥራ መጠን ዋጋቸውን ይከፍላቸዋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤ ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ኤፍሬም ነፋስን ያሰማራል፥ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዓመጻን ያበዛል፤ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብጽም ዘይት ይወስዳሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ኤፍሬም ግን ክብርንና ከንቱ ነገርን የሚያሳድድ ክፉ ጋኔን ነው። ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፤ ከአሦርም ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ ምሕረትም ያደርጉለት ዘንድ ወደ ግብፅ ዘይትን ይልካል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ኤፍሬም ነፋስን ይበላል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል፥ ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፥ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብጽም ዘይት ይወስዳሉ። 参见章节 |