Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕብራውያን 9:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 የአይሁድ የካህናት አለቃ የራሱ ያልሆነውን ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባ ነበር፤ ክርስቶስ ግን ራሱን ብዙ ጊዜ መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ አልገባም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሊቀ ካህናት የራሱ ያልሆነውን ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንደሚገባ፣ ክርስቶስ ራሱን ብዙ ጊዜ መሥዋዕት ለማድረግ ወደ ሰማይ አልገባም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት ደጋግሞ እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሊቀ ካህ​ናቱ ያደ​ር​ገው እንደ ነበረ፥ በያ​መ​ቱም ደም ይዞ ወደ ቅድ​ስት ይገባ እንደ ነበረ ዘወ​ትር ራሱን የሚ​ሠዋ አይ​ደ​ለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤

参见章节 复制




ዕብራውያን 9:25
9 交叉引用  

አሮን በዓመት አንድ ጊዜ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ከታረደው እንስሳ ደም ወስዶ በአራቱም ጒጦች ላይ በማድረግ መሠዊያው የሚነጻበትን ሥርዓት ይፈጽም፤ ይህም ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በየዓመቱ ይፈጸም፤ በዚህ ዐይነት ይህ መሠዊያ ለእግዚአብሔር በፍጹም የተቀደሰ ይሁን።”


በዚህም “ፈቃድ” በሚለው ቃል መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ አንዴ በማያዳግም ሁኔታ መሥዋዕት ሆኖ በመቅረቡ ምክንያት ተቀድሰናል።


እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! በኢየሱስ ደም አማካይነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት የሚያስችለንን መተማመኛ አግኝተናል፤


እርሱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን አንዴ በማያዳግም ሁኔታ የራሱን ደም ይዞ ገባ እንጂ የፍየሎችንና የወይፈኖችን ደም ይዞ አልገባም፤ በዚህም ዐይነት የዘለዓለም ቤዛን አስገኘልን።


በዘለዓለም መንፈስ አማካይነት ራሱን ነውር የሌለበት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እንድናገለግል ኅሊናችንን ከሞተ ሥራ እንዴት ይበልጥ ያነጻ ይሆን!


ሁለት ክፍሎች ያሉአት ድንኳን ተዘጋጅታ ነበር። መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት የነበረባት መጀመሪያይቱ ክፍል “ቅድስት” ትባል ነበር።


እንዲህማ ቢሆን ኖሮ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዘመናት መጨረሻ ኃጢአትን ለማስወገድ ራሱን መሥዋዕት በማድረግ አንዴ በማያዳግም ሁኔታ ተገልጦአል።


ወደ ሁለተኛዋ ውስጠኛ ክፍል የሚገባው ግን የካህናቱ አለቃ ብቻ ነው፤ የሚገባውም በዓመት አንድ ቀን ብቻ ነው፤ እርሱም ስለ ራሱ ኃጢአትና ሕዝቡ ባለማወቅ ስላደረገው ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም።


跟着我们:

广告


广告