Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕብራውያን 12:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ተጠንቀቁ፤ እንዲሁም ምንም መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይበቅልና እንዳያስቸግራችሁ ብዙዎችንም እንዳያረክስ ተጠንቀቁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት፣ ደግሞም መራራ ሥር በቅሎ ችግር እንዳያስከትልና ብዙዎችን እንዳይበክል ተጠንቀቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከመካከላችሁ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት መራራ ሥር በቅሎ እንዳያስጨንቃችሁ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አስ​ተ​ውሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጸጋ የሚ​ያ​ቃ​ልል አይ​ኑር፤ ሕማ​ምን የም​ታ​መጣ፥ ብዙ​ዎ​ች​ንም የም​ታ​ስ​ታ​ቸ​ውና የም​ታ​ረ​ክ​ሳ​ቸው መራራ ሥር የም​ት​ገ​ኝ​በ​ትም አይ​ኑር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥

参见章节 复制




ዕብራውያን 12:15
41 交叉引用  

ኢዮርብዓም ኃጢአት ስለሠራና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት ስለ መራ፥ እግዚአብሔር እስራኤልን ይተዋል።”


አሮንንም “ከቶ ይህ ሕዝብ ምን አድርጎህ ነው ይህን የመሰለ አስከፊ ኃጢአት እንዲሠራ ያደረግኸው?” አለው።


ልብ የሕይወት ምንጭ ስለ ሆነ ልብህን ከሁሉ ነገር አስበልጠህ ጠብቀው።


ለመሆኑ እኔ ለእርሱ ያላደረግኹለት ነገር አለን? ከዚህስ ሌላ ላደርግለት የሚገባ ምን አለ? ታዲያ፥ መልካም ፍሬ ያፈራል ብዬ ስጠብቀው ስለምን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ?


ይህም የሠራዊት አምላክ የወይን ቦታ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፤ እርሱም የይሁዳ ሕዝብ ደስ የሚሰኝበት ተክል ነው። መልካም ሥራ እንዲሠሩ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ በዚህ ፈንታ ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ፤ ቅን ፍርድ ይሰጣሉ ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ እነርሱ ግን ፍርድን በማጓደላቸው የሕዝቡ ጩኸት በዛ።


እኔ ከተመረጠ ዘር መልካም የወይን ተክል አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለውጠሽ እንደ ተበላሸ የበረሓ የወይን ተክል ሆነሻል።


ነገር ግን የአንተ እምነት እንዳይጠፋ እኔ ለአንተ እጸልያለሁ፤ እንደገና በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና።”


ስለዚህ የቆመ የሚመስለው ሰው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።


ፍቅር ያለው ሰው ምንጊዜም አይወድቅም፤ ትንቢትን የመናገር ስጦታ ያልፋል፤ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ችሎታ ያልፋል፤ ዕውቀትም ቢሆን ያልፋል።


አትታለሉ፤ “መጥፎ ጓደኛ ጥሩውን ጠባይ ያበላሻል።”


እንግዲህ መመካታችሁ መልካም አይደለም፤ ትንሽ እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው ታውቁ የለምን?


በእምነታችሁ የጸናችሁ መሆናችሁን ለማረጋገጥ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ መሆኑን አልተገነዘባችሁምን? አለበለዚያ በፈተና ወድቃችኋል ማለት ነው፤


ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ እንደ መሆናችን የተቀበላችሁትን ጸጋ በከንቱ አታስቀሩት ብለን እንለምናችኋለን።


አንዳንድ ከአይሁድ ወገን የሆኑ ክርስቲያኖችም የጴጥሮስን ግብዝነት ተከተሉ፤ በርናባስ እንኳ ሳይቀር በግብዝነታቸው ተስቦ ነበር።


እናንተ ሕግን በመጠበቅ ለመጽደቅ የምትፈልጉ ሁሉ ከክርስቶስ ተለይታችኋል፤ ከጸጋውም ርቃችኋል።


እንዲህ ዐይነቱ ነገር ለክርስቲያኖች ስለማይስማማ ዝሙት ወይም ማናቸውንም ዐይነት ርኲሰት ወይም ንፍገት ማድረግ ይቅርና ወሬው እንኳ ሊሰማባችሁ አይገባም።


በዚህ ከቆማችሁት መካከል ማንም ወንድ ወይም ሴት፥ ቤተሰብ ወይም ነገድ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ፈቀቅ በማለት የሌሎችን ሕዝቦች አማልክት የሚከተል እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ በመካከላችሁ እንደዚህ ያለ መርዘኛና መራራ የሆነ ሥራ የሚሠራ አይኑር፤


ጠላቶቻችን እንደ ሰዶምና ገሞራ የረከሱ ናቸው፤ እነርሱም መራራና መርዘኛ ፍሬ እንደሚሰጥ የወይን ተክል ናቸው።


እንግዲህ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን በዐይናችሁ ያያችሁትን ሁሉ እንዳትረሱና ከአእምሮአችሁ እንዳይጠፋ ተጠንቀቁ። ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤


ስለዚህ በእናንተ የሚገኙትን የምድራዊ ሕይወት ምኞቶች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም “ዝሙት፥ ርኲሰት፥ ፍትወት፥ ክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማምለክ የሆነ መጐምጀት” ናቸው።


ለንጹሖች፥ ሁሉ ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሶችና ለማያምኑ ሰዎች ግን ንጹሕ የሆነ ምንም ነገር የለም፤ እንዲያውም አእምሮአቸውም ሆነ ኅሊናቸው የረከሰ ነው።


ወዳጆቼ ሆይ፥ ከእናንተ መካከል ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያርቅ ክፉና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።


ስለዚህ እርሱ ወደሚሰጠን የዕረፍት ቦታ ለመግባት የተቀበልነው ተስፋ ገና የጸና ስለ ሆነ ከእናንተ ማንም ወደዚህ የዕረፍት ቦታ የመግባት ዕድል ሳያገኝ እንዳይቀር ሁላችንም እንጠንቀቅ።


ስለዚህ ማንም የእነዚያን ሰዎች አለመታዘዝ ተከትሎ እንዳይወድቅ ወደ እግዚአብሔር የዕረፍት ቦታ ለመግባት እንትጋ።


እናንተ ሁላችሁም በተስፋ የምትጠባበቁትን ነገር እስክትጨብጡ ድረስ ትጋታችሁን እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን፤


እናንተ ግን በእስራኤል ሰፈር ችግርንና ጥፋትን እንዳታስከትሉ መደምሰስ ከሚገባቸው ነገሮች ማናቸውንም ጓጒታችሁ ከመውሰድ ራሳችሁን ጠብቁ፤


ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማረጋገጥ በይበልጥ የምትጓጉ ሁኑ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም።


በስሕተት ከሚኖሩት ሰዎች መካከል አምልጠው ከመጡ ገና ብዙ ያልቈዩትን ሰዎች ከንቱ የሆነ የዕብሪት ቃል በመናገር፥ በሥጋዊ ፍትወትና በሴሰኛነት በማባበል ያታልሉአቸዋል።


እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚጠፉ ከሆነ፥ ታዲያ፥ እናንተ በቅድስናና እግዚአብሔርን በማምለክ መኖር እንዴት አይገባችሁም?


ስለዚህ ወዳጆች ሆይ! ይህ ሁሉ የሚሆንበትን ቀን በመጠባበቅ ላይ ካላችሁ፥ ጌታ ያለ ነውር ወይም ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም እንዲያገኛችሁ በትጋት ኑሩ፤


እናንተ ግን ሙሉ ዋጋችሁን ለመቀበል ትጉ፤ የሠራችሁትም እንዳይጠፋባችሁ ተጠንቀቁ።


跟着我们:

广告


广告