Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐጌ 2:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደገና ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንና የብስን አናውጣለሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በቅርቡ፣ አንድ ጊዜ እንደ ገና ሰማያትንና ምድርን፣ ባሕሩንና የብሱን አናውጣለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ እንደገና በቅርብ ጊዜ ሰማያትንና ምድርን ባሕርንና የብስን አናውጣለሁ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ገና አንድ ጊዜ በቅርብ ዘመን እኔ ሰማያትንና ምድርን ባሕርንና የብስንም አናውጣለሁ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ገና አንድ ጊዜ በቅርብ ዘመን እኔ ሰማያትንና ምድርን ባሕርንና የብስንም አናውጣለሁ፥

参见章节 复制




ሐጌ 2:6
25 交叉引用  

እግዚአብሔር ምድርን ከቦታዋ ያንቀጠቅጣል፤ ምሰሶችዋንም ያነቃንቃል።


እግዚአብሔር ስለ ተቈጣ ምድር ተናወጠች፤ ተንቀጠቀጠችም፤ የተራሮች መሠረቶች ተናጉ፤ ተነቃነቁም።


ከጥቂት ጊዜ በኋላ ክፉ አድራጊዎች ፈጥነው ይጠፋሉ፤ ብትፈልጋቸው እንኳ አታገኛቸውም።


ከጥቂት ጊዜ በኋላ በእናንተ ላይ ያለኝ ቊጣ ይቆማል፤ ከዚያን በኋላ እነርሱን እደመስሳለሁ።


እኔ የሠራዊት አምላክ ቊጣዬን በምገልጥበት ጊዜ ሰማይን አንቀጠቅጣለሁ፤ ምድርም ከስፍራዋ እንድትናወጥ አደርጋለሁ።


እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚመጣበት ጊዜ ከቊጣውና ከአስፈሪ ግርማው ለማምለጥ በአለት ዋሻና በመሬት ንቃቃት ውስጥ ለመሸሸግ ይሞክራሉ።


በጥቂት ጊዜ ውስጥ የሊባኖስ ጫካ የእርሻ ቦታ ይሆናል፤ የእርሻው ቦታ ወደ ጫካነት ይለወጣል።


ፀሐይ፥ ጨረቃና ከዋክብት ሁሉ ይጠፋሉ፤ ሰማይም እንደ ብራና ተጠቅሎ ይወገዳል፤ ከዋክብትም እንደ ወይንና እንደ በለስ ዛፍ ቅጠል ይረግፋሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ተቃርቦአል፤


ባቢሎን እንደ እህል መውቂያ አውድማ ትሆናለች፤ ሕዝብዋንም እንደሚወቃ እህል ጠላት ያበራያቸዋል። እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።”


በዚያን ቀን በእስራኤል ምድር ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደሚሆን በቅናቴና በሚነድ ቊጣዬ ዐውጃለሁ።


እያንዳንዱ የዓሣና የወፍ ዐይነት፥ እያንዳንዱም አውሬና እንስሳ በምድር የሚኖር እያንዳንዱ ሰው እኔን በመፍራቱ ይንቀጠቀጣል፤ ተራራዎች ይወድቃሉ፤ ገደሎች ተፈረካክሰው ይናዳሉ፤ እያንዳንዱም የቅጽር ግንብ ይደረመሳል።


እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በኢየሩሳሌም ሆኖ፥ የሚያስፈራ ድምፁን ያሰማል፤ ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ለእስራኤል መጠጊያ ምሽግ ይሆናል፤


በላይ በሰማይ ድንቅ ነገሮችን፥ በታች በምድር ተአምራትን አሳያለሁ፤ ደም፥ እሳት፥ የጢስ ጭጋግም ይታያል።


ለዚህም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ “ያ የሚመጣው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይመጣል፤ አይዘገይምም፤


ልዩ ልዩ ወገንና፥ ነገድ፥ ልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪዎችና ሕዝቦች ሦስት ቀን ተኩል ሬሳቸውን ይመለከታሉ፤ ሬሳቸው እንዳይቀበርም ይከለክላሉ።


跟着我们:

广告


广告