Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 9:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 የሴም አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! ከነዓንም የሴም አገልጋይ ይሁን!

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ደግሞም፤ “የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፤ ከነዓንም የሴም ባሪያ ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ደግሞም እንዲህ አለ፦ “የሴም ጌታ እግዚእብሔር ይባረክ! ከነዓንም የሴም አገልጋይ ይሁን!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እን​ዲ​ህም አለ፥ “የሴም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ረክ፤ ከነ​ዓ​ንም ለእ​ርሱ ባሪያ ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እንዲህም አለ፤ የሴም አምላክ እግዚእብሔር ይባረን፥ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 9:26
15 交叉引用  

በጠላቶችህ ላይ ድልን ያቀዳጀህ፥ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።” አብራምም በምርኮ ካገኘው ሀብት ሁሉ አንድ ዐሥረኛውን ለመልከ ጼዴቅ ሰጠው።


“ለጌታዬ ያለውን ታማኝነትና ዘለዓለማዊ ፍቅር የጠበቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በቀጥታ መርቶ ወደ ጌታዬ ዘመዶች ቤት ያመጣኝ እርሱ ነው” አለ።


መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ያገልግሉህ፤ በወንድሞችህ ሁሉ ላይ አለቃ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚመርቁህም የተመረቁ ይሁኑ።”


ይስሐቅም “ቀደም ብዬ እርሱን የአንተ ጌታ አድርጌዋለሁ፤ ወንድሞቹ ሁሉ የእርሱ አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጌአለሁ፤ እህልና የወይን ጠጅ እንዲበዛለት አድርጌአለሁ፤ ልጄ ሆይ! እንግዲህ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?” አለው።


በሰይፍህ ኀይል ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ፤ በተቃወምከው ጊዜ ግን ከእርሱ ጭቈና ትላቀቃለህ።”


እንደዚህ የሚሆንለት ሕዝብ የተባረከ ነው! እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለት ሕዝብ የተባረከ ነው!


እነርሱ በትውልዳቸው ከነገድ አባቶች የመጡ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የመጣው ከእነርሱ ዘር ነው፤ እርሱ ከሁሉ በላይ ነው፤ ለዘለዓለምም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን!


የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በሰማያዊ ግርማው አንተን ለመርዳት በሰማይና በደመና ላይ እንደ እኛ አምላክ እንደ እግዚአብሔር ማንም የለም


አሁን ግን የሚበልጠውን፥ በሰማይ ያለውን አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው “አምላካችን” ብለው ቢጠሩት አያሳፍረውም።


ይህን በማድረጋችሁ ምክንያት እግዚአብሔር ፈርዶባችኋል፤ ስለዚህም የእናንተ ሕዝብ እንጨት በመቊረጥና ውሃ በመቅዳት ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለዘለዓለም አገልጋዩ ይሆናል።”


እስራኤላውያን ብርታት ባገኙ ጊዜ ከነዓናውያን ለእነርሱ የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ያስገድዱአቸው ነበር፤ ሆኖም ሁሉንም አላስወጡም ነበር።


跟着我们:

广告


广告