Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 50:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ባለ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ተከትለውት ወጡ፤ በጠቅላላው የተከተለው አጀብ እጅግ ብዙ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እንዲሁም ሠረገሎችና ፈረሰኞች ዐብረውት ወጡ፤ አጀቡም እጅግ ብዙ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሰረጎሎችም ፈረሰኞችም ከእርሱ ጋር ወጡ፥ ሠራዊቱም እጅግ ብዙ ነበረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሰረ​ገ​ሎ​ችም፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ወጡ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ብዙ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሰረጎሎችም ፈረሶኞችም ከእርሱ ጋር ወጡ ሠራዎቱም እጅግ ብዙ ነበረ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 50:9
10 交叉引用  

በንጉሡ ሁለተኛ ሠረገላ ላይ እንዲቀመጥ አደረገው፤ የንጉሡም የክብር ዘብ ከፊት ፊት እየሄደ “እጅ ንሡ! እጅ ንሡ!” ይል ነበር፤ ዮሴፍ በግብጽ ምድር ላይ አስተዳዳሪ ሆኖ የተሾመው በዚህ ዐይነት ነበር።


ዮሴፍ አባቱን ለመገናኘት በሠረገላው ተቀምጦ ወደዚያ ሄደ፤ በተገናኙም ጊዜ ዮሴፍ በአባቱ አንገት ላይ ተጠምጥሞ ለብዙ ጊዜ አለቀሰ።


ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ “አጣድ” ተብላ ወደምትጠራው አውድማ ደረሱ፤ እዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ አለቀሱ፤ ዮሴፍም እዚያ ሰባት ቀን ሙሉ የሐዘን ውሎ አደረገ።


እንዲሁም የዮሴፍ ቤተሰቦች፥ ወንድሞቹና ሌሎችም የአባቱ ቤተሰቦች ሁሉ ከዮሴፍ ጋር ሄዱ፤ በጌሴም የቀሩት ሕፃናት ልጆቻቸው፥ በጎቻቸው፥ ፍየሎቻቸውና ከብቶቻቸው ብቻ ነበሩ።


አንተ እኮ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ከሆነው ከአሦር ተራ የጦር መኰንን ጋር እንኳ መወዳደር አትችልም፤ ግብጻውያን ሠረገሎችንና ፈረሶችን ይልኩልኛል ብለህ የምትጠባበቀውም በዚሁ ምክንያት ነው።


የግብጻውያንን ልብ ስለማደነድን ሕዝቡን ያሳድዳሉ፤ ንጉሡንና ሠራዊቱን፥ ሠረገሎቹንና ፈረሰኞቹን ድል በመንሣት ክብርን እጐናጸፋለሁ።


ውሃውም ተመልሶ እስራኤላውያንን ይከተሉ የነበሩትን ሠረገሎችን፥ ፈረሰኞችንና መላውን የግብጽ ሠራዊት ሸፈነ፤ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ አልተረፈም።


ስድስት መቶ ምርጥ ሠረገሎችን ጨምሮ በግብጽ ያሉትን ሠረገሎች ሁሉ አሰለፈ፤ የጦር አዛዦችንም መደበላቸው፤


ውዴ ሆይ! የፈርዖንን ሠረገሎች በሚስቡ ፈረሶች መካከል ያለችውን ውብ ባዝራ ትመስያለሽ፤


አንዳንድ መንፈሳውያን ሰዎች እስጢፋኖስን ቀበሩት፤ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ አለቀሱለት።


跟着我们:

广告


广告