Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 49:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ይሁን እንጂ እንደ ውሃ የምትዋልል ስለ ሆንክ፥ የበላይ አለቅነት ለአንተ አይገባም፤ ወደ አባትህ አልጋ ወጥተሃል፤ የአባትህንም ቁባት ደፍረሃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እንደ ውሃ የዋለልህ ነህና እልቅና አይኖርህም፤ የአባትህን መኝታ ደፍረሃል፤ ምንጣፌንም አርክሰሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እንደ ውኃ የምትዋልል፥ አለቅነት ለአንተ አይሁን፥ ወደ አባትህ መኝታ ወጥተሃልና፥ አረከስኽውም፥ ወደ አልጋዬም ወጣ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እንደ ውኃ የሚ​ዋ​ልል ነው፤ ኀይል የለ​ውም፤ ወደ አባቱ መኝታ ወጥ​ቶ​አ​ልና፤ ያን ጊዜ የወ​ጣ​በ​ትን አልጋ አር​ክ​ሶ​አ​ልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እንደ ውኅ የምትዋልል ነህ አለቅነት ለአንተ አይሁን፤ ወደ አባትህ መኝታ ወጥተሃልና፤ አረከስኽውም ወደ አልጋዬም ወጣ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 49:4
11 交叉引用  

ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው።


ከእስራኤል ጋር ወደ ግብጽ የወረዱት የእስራኤላውያን ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የያዕቆብ የበኲር ልጅ ሮቤል፥


የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች ቀጥሎ የተመለከቱት ናቸው፤ (ሮቤል የአባቱን አልጋ ደፍሮ በማርከሱ የብኲርናውን መብት ስላጣ፥ ያ መብት ለዮሴፍ ተሰጥቶ ነበር፤


በመካከላችሁ አሳፋሪ የዝሙት ሥራ መኖሩ ይወራል፤ እንዲህ ዐይነቱ የዝሙት ሥራ በአሕዛብ ዘንድ እንኳ የማይደረግ ነው፤ ይኸውም የእንጀራ እናቱን እንደ ሚስት አድርጎ የሚኖር አለ ተብሎአል።


“ ‘የአባቱ ሚስቶች ከሆኑት ከየትኛዋም ጋር ግንኙነት በማድረግ የአባቱን ክብር የሚያዋርድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።


ሙሴ ሰለ ሮቤል ነገድ እንዲህ አለ፦ “ምንም እንኳ ብዛቱ ጥቂት ቢሆን፥ ጌታ ሆይ የሮቤል ነገድ ይኑር እንጂ አይሙት።”


“ ‘የሌላውን ሰው ሚስቱን፥ ቤቱን፥ ርስቱን፥ አገልጋዮቹን፥ ከብቱን፥ አህዮቹንም ሆነ ማናቸውንም ንብረቱን ሁሉ አትመኝ።’


ኃጢአት ከማድረግ የማይቈጠብ ቅንዝረኛ ዐይን አላቸው፤ የኃጢአት መሥራት ፍላጎታቸው መቼም አይረካም፤ በእምነት ጸንተው ያልቆሙትን ሰዎች ያታልላሉ፤ ለገንዘብ ይስገበገባሉ። የተረገሙ ሰዎች ናቸው።


እርሱ ስለዚህ ጉዳይ በመልእክቶቹ ሁሉ በዚሁ ዐይነት ጽፎአል፤ በመልእክቶቹ ውስጥ አንዳንድ ለመረዳት የሚያስቸግሩ ነገሮች አሉ። ዕውቀት የጐደላቸውና ወላዋዮች ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህንም ነገሮች ያጣምማሉ፤ ይህንንም የሚያደርጉት ለጥፋታቸው ነው።


跟着我们:

广告


广告