Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 48:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለዚህ በዚያን ቀን እንዲህ ሲል ባረካቸው፤ “እስራኤላውያን በሚመርቁበት ጊዜ የእናንተን ስም በማስታወስ፥ ‘እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርጋችሁ’ ይላሉ።” በዚህ አኳኋን ያዕቆብ ኤፍሬምን ከምናሴ አስቀደመው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በዚያ ዕለት ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “በአንተ ስም እስራኤል እንዲህ ብሎ ይመርቃል፤ ‘እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርጋችሁ።’ ” በዚህ ሁኔታም ኤፍሬምን ከምናሴ አስቀደመው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ስለዚህ በዚያን ቀን እንዲህ ሲል ባረካቸው፤ “እስራኤላውያን በሚመርቁበት ጊዜ የእናንተን ስም በማስታወስ፥ ‘እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርጋችሁ’ ይላሉ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ብሎ ባረ​ካ​ቸው፥ “በእ​ና​ንተ እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ተብሎ ይባ​ረ​ካል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ኤፍ​ሬ​ምና እንደ ምናሴ ይባ​ር​ክህ።” ኤፍ​ሬ​ም​ንም ከም​ናሴ ፊት አደ​ረ​ገው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በዚያም ቀን እንዲህ ብሎ ባረካቸው፦ በእናንተ እስራኤል እንዲህ ብሎ ይባርካል፦ እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርግህ። ኤፍሬምንም ከምናሴ ፊት አደረገው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 48:20
13 交叉引用  

“አንቺ እኅታችን የብዙ ሺህ ሕዝብ እናት ሁኚ፤ ዘሮችሽም የጠላቶቻቸውን ከተሞች ይውረሱ!” ብለው ርብቃን መረቁአት።


ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ይባርክህ! ብዙ ልጆችም ይስጥህ! የብዙ ሕዝቦችም አባት ያድርግህ!


ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ ወደ ቀድሞ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤


ከዮሴፍ ነገድ (እርሱም ከምናሴ ነገድ) የሱሲ ልጅ ጋዲ፥


እንግዲህ የአገሪቱን ሁኔታ አጥንተው እንዲመለሱ ሙሴ የላካቸው ሰዎች እነዚህ ነበሩ፤ የነዌን ልጅ ሆሼዓን “ኢያሱ” ብሎ ስሙን ለወጠው።


ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ ሆሼዓ


በሰባተኛው ቀን መባውን ያቀረበው ከኤፍሬም ነገድ የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማዕ ነበር።


በስምንተኛው ቀን መባውን ያቀረበው ከምናሴ ነገድ የፍዳጹር ልጅ ገማልኤል ነበር።


ያዕቆብ የሚሞትበት ጊዜ ሲቃረብ የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸውን የባረካቸውና በብትሩ ጫፍ ተደግፎ የሰገደው በእምነት ነው።


የዮሴፍ ነገድ ወደ ኢያሱ ቀርበው “እግዚአብሔር ባርኮን ለበዛነው ለእኛ እንዴት አንድ ዕጣ ብቻ ሰጠኸን?” ብለው ጠየቁት።


跟着我们:

广告


广告