Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 48:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የያዕቆብ ዐይኖች በእርጅናው ምክንያት ስለ ደከሙ አጥርቶ ማየት አይችልም ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን ወደ እርሱ አቀረበለት፤ እርሱም ዕቅፍ አድርጎ ሳማቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዚህ ጊዜ እስራኤል ዐይኖቹ በእርጅና ምክንያት በመድከማቸው አጥርቶ ማየት ይሳነው ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን አባቱ ዘንድ አቀረባቸው፤ አባቱም ስሞ ዐቀፋቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የእስራኤልም ዐይኖች ከሽምግልና የተነሣ ደክመው ነበር፥ ማየትም አይችልም ነበር፥ ወደ እርሱም አቀረባቸው፥ ሳማቸውም፥ አቀፋቸውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዐይ​ኖች ከሽ​ም​ግ​ልና የተ​ነሣ ከብ​ደው ነበር፤ ማየ​ትም አይ​ች​ልም ነበር፤ ወደ እር​ሱም አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ ሳማ​ቸ​ውም፤ አቀ​ፋ​ቸ​ውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የእስራኤልም ዓይኖች ከሸምግልና የተነሣ ከብደው ነበር። ማየትም አይችልም ነበር ወደ እርሱም አቀረባቸው ሳማቸውም አቀፋቸውም።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 48:10
13 交叉引用  

ይስሐቅ አርጅቶ ዐይኖቹም ፈዘው ነበር፤ ታላቁን ልጁን ዔሳውን “ልጄ ሆይ!” ብሎ ጠራው፤ ልጁም “እነሆ፥ አለሁ!” አለ።


ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው። ይስሐቅ የያዕቆብን ልብስ ባሸተተ ጊዜ እንዲህ ሲል መረቀው፥ “እነሆ የልጄ መልካም ሽታ፥ እግዚአብሔር እንደ ባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤


በማግስቱ ላባ ጥዋት በማለዳ ተነሥቶ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን በመሳምና በመመረቅ ተሰናበታቸው፤ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ።


ዮሴፍ የቀሩትንም ወንድሞቹን አንድ ባንድ እየሳመ አለቀሰ፤ ከዚህ በኋላ ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር መነጋገር ጀመሩ።


ዮሴፍንም “አንተን እንደገና አያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ እግዚአብሔር ግን አንተን ብቻ ሳይሆን ልጆችህንም ጭምር አሳየኝ” አለው።


ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች ባየ ጊዜ “እነዚህ ልጆች እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀ።


በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ “አባትና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። ኤልያስም “እሺ፥ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም!” ሲል መለሰለት።


የምትተማመንባቸው ክንዶችህ ይንቀጠቀጣሉ፤ አሁን ብርቱ የሆኑ እግሮችህ ይዝላሉ፤ ጥርሶችህ ቊጥራቸው ከማነሳቸው የተነሣ ምግብ ማኘክ አይችሉም፤ ዐይኖችህ ከመፍዘዛቸው የተነሣ አጥርተው ማየት ይሳናቸዋል።


እግዚአብሔር ሰውን ማዳንና ጸሎትን መስማት የሚሳነው አይደለም።


ቀጥሎም “እንዳያዩ፥ እንዳይሰሙና እንዳያስተውሉ በዓይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸው አስተውለው ወደ እኔ ተመልሰው እንዳይፈወሱ ይህን ሕዝብ ልቡ የደነደነ፥ ጆሮው የተደፈነ፥ ዐይኑም የተጨፈነ እንዲሆን አድርግ” አለኝ።


ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ኻያ ዓመት ነበር፤ ነገር ግን ዐይኑ ያልፈዘዘና ጒልበቱም ያልደከመ ገና ብርቱ ሰው ነበር።


በእርጅና ምክንያት ዐይኖቹ ፈዘው የነበሩት ዔሊ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ሌሊት በመኝታ ክፍሉ ተኝቶ ነበር።


በዚያን ዘመን ዔሊ የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበር፤ ዐይኑም ፈዞ ነበር።


跟着我们:

广告


广告