Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 45:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የዮሴፍ ወንድሞች መምጣት በፈርዖን ቤተ መንግሥት በተሰማ ጊዜ ፈርዖንና ባለሥልጣኖቹ ደስ አላቸው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የዮሴፍ ወንድሞች መምጣት በፈርዖን ቤተ መንግሥት በተሰማ ጊዜ፣ ፈርዖንና ሹማምቱ ሁሉ ደስ አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በፈርዖንም ቤት፥ “የዮሴፍ ወንድሞች መጡ ተብሎ ወሬ ተሰማ፥” በሰሙትም ነገር ፈርዖንና አገልጋዮቹ ደስ ተሰኙበት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በፈ​ር​ዖ​ንም ቤት፥ “የዮ​ሴፍ ወን​ድ​ሞች መጡ” ተብሎ ወሬ ተሰማ፤ ፈር​ዖ​ንና ቤተ ሰቡም ሁሉ ደስ አላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በፈርዖን ቤት፦ የዮሴፍ ወንድሞች መጡ ተብሎ ወሬ ተሰማ በዚያውም ፈርዖንና ሎላልቱ ደስ ተሰኙበት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 45:16
15 交叉引用  

አብራምም “መልካም ነው፤ እርስዋ የአንቺ አገልጋይ ስለ ሆነች በቊጥጥርሽ ሥር ናት፤ የፈለግሺውን ነገር አድርጊ” አላት። ከዚህ በኋላ ሣራይ አጋርን እጅግ ስላሠቃየቻት አጋር ከቤት ወጥታ ኰበለለች።


አብርሃምን “እነሆ የእኔ ግዛት በፊትህ ነው፤ በፈለግከው ስፍራ ኑር” አለው።


ይህም አባባል ለሐሞርና ለልጁ ለሴኬም መልካም መስሎ ታያቸው፤


“እንግዲህ ጥበብና ማስተዋል ያለውን ሰው መርጠህ በአገሪቱ አስተዳዳሪ አድርገህ ሹመው፤


ዕቅዱም ለፈርዖንና ለባለሟሎቹ ሁሉ መልካም ሆኖ ታያቸው፤


ዮሴፍ የቀሩትንም ወንድሞቹን አንድ ባንድ እየሳመ አለቀሰ፤ ከዚህ በኋላ ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር መነጋገር ጀመሩ።


ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “ወንድሞችህ አህዮቻቸውን ጭነው ወደ ከነዓን እንዲመለሱ ንገራቸው፤


ሕዝቡም ሁሉ ይህን ነገር ተመልክተው ደስ አላቸው፤ በእርግጥም ንጉሡ ያደረገው ነገር ሁሉ ሕዝቡን ደስ አሰኛቸው።


ንጉሡና ሕዝቡም በዚሁ ዕቅዳቸው ደስ ተሰኙ።


ንጉሡና ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖች ሁሉ ይህን ሐሳብ በደስታ ተቀበሉት፤ ንጉሡም መሙካን ያቀረበውን ምክር በሥራ ላይ አዋለ።


ከእነርሱም መካከል በይበልጥ የምትወዳትን መርጠህ በአስጢን እግር ተተክታ ንግሥት እንድትሆን አድርግ።” ንጉሡም ይህ ምክር መልካም መሆኑን ተመልክቶ በሥራ ላይ አዋለው።


ስለዚህ ሚስቱና ወዳጆቹ ሁሉ “ርዝመቱ ኻያ ሁለት ሜትር የሆነ መስቀያ እንጨት አዘጋጅተህ ነገ ጠዋት መርዶክዮስን ለመስቀል የንጉሡን ፈቃድ መጠየቅ ትችላለህ፤ ከዚያም በኋላ ደስ ብሎህ ወደ ግብዣው ትሄዳለህ” ሲሉ ሐሳብ አቀረቡለት። ሃማንም ሐሳቡ መልካም እንደ ሆነ ተቀብሎ የመስቀያውን እንጨት አዘጋጀ።


ይህ አባባል ሁሉንም አስደሰተ ቀጥሎ ያሉትም ሰዎች ተመረጡ፤ እነርሱም በእምነትና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ እስጢፋኖስን፥ ፊልጶስ፥ ጵሮኮሮስ፥ ኒቃሮና፥ ጢሞና፥ ጰርሜና የአይሁድን እምነት ተቀብሎ የነበረው የአንጾኪያው ኒቆላዎስ ናቸው።


ዳግመኛ ወደ ግብጽ ተመልሰው በሄዱ ጊዜ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ተገለጠ፤ ቤተ ዘመዱም በፈርዖን ዘንድ ታወቀ።


跟着我们:

广告


广告