Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 43:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እነርሱም “ሰውየው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተሰባችን አጥብቆ መረመረን፤ ‘አባታችሁ በሕይወት አለን? ሌላስ ወንድም አላችሁን?’ ብሎ ጠየቀን፤ እኛም ለጥያቄው ተገቢውን መልስ ሰጠን፤ ስለዚህ ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ እንድትመጡ’ እንደሚለን እንዴት ልናውቅ እንችል ነበር?”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነርሱም፣ “ሰውየው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተ ሰባችን አጥብቆ ጠየቀን፤ እንደ ገናም ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ?’ ሲል ጠየቀን። እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው። ታዲያ፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደዚህ እንድትመጡ’ እንደሚል እንዴት ማወቅ እንችል ነበር?” ብለው መለሱለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እነርሱም፥ “ሰውየው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተሰባችን አጥብቆ ጠየቀን፤ እንደገናም ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ’ ሲል ጠየቀን። እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው። ታድያ፥ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደዚህ እንድትመጡ’ እንደሚል እንዴት ማወቅ እንችል ነበር?” ብለው መለሱለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነ​ር​ሱም አሉ፥ “ያ ሰው ስለ እኛና ስለ ትው​ል​ዳ​ችን ፈጽሞ ጠየ​ቀን፤ እን​ዲ​ህም አለን፦ ‘ሽማ​ግ​ሌው አባ​ታ​ችሁ ገና በሕ​ይ​ወት ነው? ወን​ድ​ምስ አላ​ች​ሁን?’ እኛም እን​ደ​ዚሁ እንደ ጠየ​ቀን መለ​ስ​ን​ለት፤ በውኑ፦ ‘ወን​ድ​ማ​ች​ሁን አምጡ’ እን​ዲ​ለን እና​ውቅ ነበ​ርን?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እነርሱም አሉ፦ ያ ሰው ስለ እኛና ስለ ወገናችን ፈጽሞ ጠየቀን እንዲህም አለን፦ አባታችሁ ገና በሕይወት ነው? ወንድምስ አላችሁን? እኛም እንደዚሁ እንደ ጥያቄው መለስንለት በውኑ፦ ወንድማችሁን አምጡ እንዲለን እናውቅ ነበርነን?

参见章节 复制




ዘፍጥረት 43:7
6 交叉引用  

“እኛ ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን፤ እኛ የምንታመን ነን፤ ሰላዮችም አይደለንም” አሉት።


እነርሱም “እኛ አገልጋዮችህ በከነዓን ምድር የሚኖር የአንድ ሰው ልጆች የሆንን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ አንዱ ወንድማችን ሞቶአል፤ የመጨረሻ ታናሽ ወንድማችን አሁን ከአባታችን ጋር ይገኛል” አሉት።


እርሱም ስለ ደኅንነታቸው ከጠየቃቸው በኋላ “ያ የነገራችሁኝ ሽማግሌ አባታችሁ እንዴት ነው? አሁንም በሕይወት አለን?” አላቸው።


ይሁዳ ግን ለአባቱ እንዲህ ብሎ መለሰለት፥ “ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ እፊቴ እንዳትቀርቡ’ በማለት በብርቱ አስጠንቅቆናል፤


ያዕቆብም “ ‘ሌላ ወንድም አለን’ ብላችሁ ለሰውየው በመናገር ለምን ይህን ያህል መከራ አመጣችሁብኝ?” አለ።


ጌታዬ ከአሁን ቀደም ‘አባት አላችሁ ወይ? ሌላ ወንድምስ አላችሁ ወይ?’ ብለህ ጠየቅከን፤


跟着我们:

广告


广告