Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 42:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እናንተ ታማኞች ሰዎች ከሆናችሁ ከእናንተ አንዱ እዚሁ በእስር ቤት ይቈይ፤ የቀራችሁት እህሉን ይዛችሁ ወደ ተራቡት ዘመዶቻችሁ ሂዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ታማኝ ሰዎች ከሆናችሁ፣ ከመካከላችሁ አንዱ እዚህ እስር ቤት ሲቈይ፣ የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተ ሰቦቻችሁ እህል ትወስዱላቸዋላችሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ታማኝ ሰዎች ከሆናችሁ፥ ከመካከላችሁ አንዱ እዚህ እስር ቤት ሲቈይ፥ የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተሰቦቻችሁ እህል ትወስዱላቸዋላችሁ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እና​ንተ ሰላ​ማ​ው​ያን ከሆ​ና​ችሁ ከእ​ና​ንተ አንዱ ወን​ድ​ማ​ችሁ በግ​ዞት ቤት ይታ​ሰር፤ እና​ንተ ግን ሂዱ፤ የሸ​መ​ታ​ች​ሁ​ትን እህ​ልም ውሰዱ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እናንተ የታመናችሁ ከሆናችሁ ከእናንተ አንዱ ወንድማችሁ በግዞታችሁ ቤት ይታስር እናንተ ግን ሂዱ እህሉንም ለቤታችሁ ራብ ውሰዱ

参见章节 复制




ዘፍጥረት 42:19
13 交叉引用  

ስለዚህ ዮሴፍ ታስሮ ወደሚገኝበት ወደ ዘበኞች አለቃ ቤት ተወስደው እንዲታሰሩ አደረገ።


ራቡ በመላው ግብጽ እየተስፋፋና እየበረታ ስለ ሄደ፥ ዮሴፍ ጐተራዎቹ ሁሉ ተከፍተው እህሉ ለግብጻውያን እንዲሸጥላቸው አደረገ።


“እኛ ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን፤ እኛ የምንታመን ነን፤ ሰላዮችም አይደለንም” አሉት።


በሦስተኛው ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው ስለ ሆንኩ እንዲህ ብታደርጉ ሕይወታችሁን ታድናላችሁ፤


ከዚህ በኋላ ታናሽ ወንድማችሁን ይዛችሁልኝ ኑ፤ በዚህ ዐይነት የተናገራችሁት ሁሉ እውነት መሆኑ ይረጋገጣል፤ ከመሞትም ትድናላችሁ።” እነርሱም በዚህ ነገር ተስማሙ፤


የዮሴፍ ወንድሞች የገዙትን እህል በአህዮቻቸው ጭነው ጒዞ ጀመሩ።


ሰውየውም እንዲህ አለን፤ ‘ታማኞች ሰዎች መሆናችሁን የማውቀው ይህን አንድ ነገር ብታደርጉ ነው፤ ይኸውም ከእናንተ አንዱ ከእኔ ጋር ይቈይ፤ ሌሎቻችሁ ለተራቡት ቤተሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁ ወደ አገራችሁ ተመለሱ፤


ለአባቱም በዐሥር አህዮች የተጫነ ከግብጽ ምድር የሚገኘውን መልካም ነገር ሁሉ ላከለት፤ እንዲሁም በሚመጣበት ጊዜ ለስንቅ የሚሆነው በሌሎች ዐሥር እንስት አህዮች የተጫነ እህል፥ ዳቦና ሌላም ምግብ ላከለት።


ሕዝቡ ግን ተዘርፈውና ተበዝብዘው በዋሻ ውስጥ ተዘግቶባቸዋል፤ በወህኒ ቤትም ተሸሽገዋል። ተዘረፉ፤ ተበዘበዙ፤ ማንም በመታደግ ሊያድናቸው አልቻለም።


ስለዚህ የዕውሮችን ዐይን ታበራለህ፤ በጨለማው ጒድጓድ እስር ቤት ውስጥ ያሉትን እስረኞችን ታወጣለህ።


እነርሱም በብርቱ ተቈጥተው ካስደበደቡኝ በኋላ የእስር ቤት እንዲሆን አድርገውት ወደነበረው ወደ ጸሐፊው ወደ ዮናታን ቤት ውስጥ አስገብተው ዘጉብኝ፤


跟着我们:

广告


广告