ዘፍጥረት 39:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 እስማኤላውያን ነጋዴዎች ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት፤ እዚያም ከግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ ለሆነው ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር የተባለው ግብጻዊ፥ የፈርዖን የዘበኞች አለቃ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ወደ ግብጽ ተወስዶ ነበር፤ ከፈርዖን ሹማምት አንዱ የሆነውም የዘበኞች አለቃ፣ ግብጻዊው ጲጥፋራ ወደዚያ ከወሰዱት ከእስማኤላውያን ነጋዴዎች እጅ ገዛው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ወደ ግብጽ ተወስዶ ነበር፤ ከፈርዖን ሹማምንት አንዱ የሆነውም የዘበኞች አለቃ፥ ግብፃዊው ጲጥፋራ ወደዚያ ከወሰዱት ከእስማኤላውያን ነጋዴዎች እጅ ገዛው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈርዖን ጃንደረባ የመጋቢዎቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ወደ ግብፅ ከአወረዱት ከይስማኤላውያን እጅ ገዛው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ዺጥፋራ ወደ ግብፅ ካወረዱት ከእስማኤላዉያን እጅ ገዛው። 参见章节 |