Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 37:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እስራኤልም ዮሴፍን “እነሆ፥ ወንድሞችህ መንጋውን ይዘው ወደ ሴኬም መሰማራታቸውን ታውቃለህ፤ ስለዚህ ወደ እነርሱ ልልክህ እፈልጋለሁ” አለው። ዮሴፍም “እሺ እሄዳለሁ” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እስራኤልም ዮሴፍን “እንደምታውቀው ወንድሞችህ መንጎቹን በሴኬም አካባቢ አሰማርተዋል፤ በል ተነሥ፣ ወደ እነርሱ ልላክህ።” አለው። ዮሴፍም “ይሁን ዕሺ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እስራኤልም ዮሴፍን፦ “ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን እየጠበቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እንድልክህ ና” አለው። እርሱም “እነሆኝ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ወን​ድ​ሞ​ችህ በሴ​ኬም በጎ​ችን የሚ​ጠ​ብቁ አይ​ደ​ሉ​ምን? ወደ እነ​ርሱ እል​ክህ ዘንድ ና” አለው። እር​ሱም፥ “እሺ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እስራኤልም ዮሴፍን፦ ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን የሚጠብቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እልክህ ዘንድ ና አለው። እርሱም እነሆኝ አለው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 37:13
13 交叉引用  

ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም “አብርሃም!” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” ብሎ መለሰ።


ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ “አብርሃም! አብርሃም!” ብሎ ጠራው። አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” አለ።


ይስሐቅ አርጅቶ ዐይኖቹም ፈዘው ነበር፤ ታላቁን ልጁን ዔሳውን “ልጄ ሆይ!” ብሎ ጠራው፤ ልጁም “እነሆ፥ አለሁ!” አለ።


ያዕቆብም ወደ አባቱ ሄደና “አባባ!” አለው፤ እርሱም “እነሆ፥ አለሁ! ለመሆኑ አንተ የትኛው ልጄ ነህ?” አለ።


ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም በሰላም ደረሰ፤ እዚያም በከተማይቱ ፊት ለፊት በሚገኘው ሜዳ ላይ ሰፈረ።


አንድ ቀን የዮሴፍ ወንድሞች የአባታቸውን መንጋዎች ይዘው ወደ ሴኬም ተሰማሩ፤


“እነሆ! እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልኆች፥ እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ።


ከዚህም በኋላ የወይኑ ተክል ባለቤት፦ ‘እንግዲህ ምን ላድርግ? የምወደውን ልጄን እልከዋለሁ፤ እርሱን ምናልባት ያከብሩት ይሆናል!’ አለ።


ዔሊ ግን ሳሙኤልን “ልጄ ሳሙኤል ሆይ!” ሲል ጠራው። ሳሙኤልም “እነሆ አለሁ ጌታዬ!” ሲል መለሰ።


እግዚአብሔርም እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ሳሙኤልን ጠራው፤ ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ “እነሆ! ስለጠራኸኝ መጥቻለሁ” አለው። ከዚህም በኋላ ሳሙኤልን ይጠራው የነበረው እግዚአብሔር መሆኑን ዔሊ ተገነዘበ፤


跟着我们:

广告


广告