Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 34:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ሆኖም እነዚህ ሰዎች አብረውን ለመኖርና ከእኛም ጋር አንድ ሕዝብ ለመሆን ፈቃደኞች የሚሆኑት ወንዶች የሆንን ሁሉ እንደ እነርሱ ለመገረዝ የተስማማን እንደ ሆነ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሆኖም ሰዎቹ ከእኛ ጋራ እንደ አንድ ሕዝብ ሆነው ዐብረውን ለመኖር ፈቃደኞች የሚሆኑት፣ የእኛ ወንዶች እንደ እነርሱ የተገረዙ እንደ ሆነ ብቻ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ነገር ግን አንድ ሕዝብ ሆነን ከእኛ ጋር ይቀመጡ ዘንድ በዚህ ነገር ብቻ እሺ ይሉናል፥ እርሱም እነርሱ እንደ ተገረዙ ወንዶቻችንን ሁሉ ብንገርዝ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እነ​ርሱ እንደ እኛ ይሆኑ ዘንድ በዚህ ብቻ እን​ም​ሰ​ላ​ቸው። አንድ ወገ​ንም እን​ሁን፤ እነ​ርሱ እን​ደ​ሚ​ገ​ርዙ ወን​ዶ​ቻ​ች​ንን ሁሉ እን​ገ​ር​ዛ​ለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ነገር ግን አንድ ሕዝብ ሆነን ከእኛ ጋር ይቀመጡ ዘንድ በዚህ ነገር ብቻ እሺ ይሉናል እነርሱ እንደ ተገረዙ ወንዶቻችንን ሁሉ ብንገርዝ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 34:22
3 交叉引用  

አንተና ከአንተ በኋላ የሚመጣው ዘርህ የምትጠብቁት ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ በመካከላችሁ ያሉት ወንዶች ሁሉ መገረዝ አለባቸው፤


“እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር የሚኖሩት በሰላም ነው፤ በምድሪቱ ላይ አብረውን ይቀመጡ፤ በነጻም ይዘዋወሩባት፤ እነሆ፥ ምድሪቱ ለእኛም ለእነርሱም ትበቃናለች፤ የእነርሱን ሴቶች ልጆች እናግባ፤ የእኛንም ሴቶች ልጆች እንዳርላቸው።


እንዲህ ብናደርግ መንጋዎቻቸውና ከብቶቻቸው፥ ሌላውም ንብረታቸው ሁሉ የእኛ ይሆን የለምን? ስለዚህ ከእነርሱ ጋር ስምምነት እናድርግ፤ እነርሱም ከእኛ ጋር ይኑሩ።”


跟着我们:

广告


广告