Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 32:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እነሆ፥ አሁን ብዙ ከብቶች፥ አህዮች፥ በጎችና ፍየሎች እንዲሁም አሽከሮችና ገረዶች አሉኝ፤ ይህን መልእክት የላክሁብህ በአንተ ዘንድ ሞገስ አገኛለሁ በሚል ተስፋ ነው።’ ”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከብቶች፣ አህዮች፣ የበግና የፍየል መንጎች እንደዚሁም የወንድና የሴት አገልጋዮች አሉኝ፤ አሁንም ይህን መልእክት ለጌታዬ መላኬ በጎ ፈቃድህን እንዳገኝ በማሰብ ነው።” ’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “በሬዎች፥ አህዮች፥ በጎች፥ ወንድ አገልጋዮች፥ እና ሴት አገልጋዮችም አገኘሁ፥ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ ለጌታዬ ለማሳወቅ ላኩብህ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ላሞ​ች​ንም፥ ግመ​ሎ​ች​ንም፥ አህ​ዮ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም፥ ወን​ዶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ንም፥ ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ንም አገ​ኘሁ፤ አሁ​ንም በፊ​ትህ ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው ለመ​ን​ገር ላክሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ላሞችንም አህዮችንም፥ በጎችን፥ ወንዶች ባሪያዎችንም ሴቶች ባሪያዎችን፥ አገኘሁ፤ አሁን፥ በፍትህ ሞገስን አገኝ ዘንድ ለጌታዬ ለማስታወቅ ላክሁ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 32:5
13 交叉引用  

በዚህ አኳኋን ያዕቆብ እጅግ ባለ ጸጋ ሆነ፤ ብዙ መንጋዎች፤ ሴቶችና ወንዶች አገልጋዮች፥ ብዙ ግመሎችና አህዮችም ነበሩት።


አሁንም እግዚአብሔር ከአባታችን ወስዶ ለአንተ የሰጠህ ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ሁሉ አድርግ።”


በዚህን ጊዜ እግዚአብሔር ያዕቆብን “ወደ አባቶችህና ወደ ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው።


ስለዚህ እባክህ ይህን ያቀረብኩልህን ስጦታ ተቀበለኝ፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሚያስፈልገኝን ሁሉ ሰጥቶኛል” አለ። ስጦታውን እንዲቀበለው ያዕቆብ ዔሳውን አጥብቆ ለመነው። እርሱም ተቀበለው።


ዔሳውም “እንግዲያውስ ከእኔ ሰዎች ጥቂቶቹን ከአንተ ጋር ላስቀርልህ” አለው። ያዕቆብ ግን “በጌታዬ ፊት ሞገስ ካገኘሁ ሌላ ምንም ነገር አያስፈልገኝም” አለው።


ዔሳውም “እፊት እፊትስ እየተነዳ ሲሄድ ያየሁት የእንስሶች መንጋ ምንድን ነው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እርሱ በአንተ ፊት ሞገስ እንዳገኝ የላክሁልህ ነው” አለ።


ሕዝቡም “ጌታችን ሆይ፥ ሕይወታችንን ስላዳንክልንና መልካም ነገር ስላደረግህልን ሁላችንም የፈርዖን ባሪያዎች እንሆናለን” አሉት።


ንጉሡም ጺባን “የመፊቦሼት የነበረው ንብረት ሁሉ ከእንግዲህ የአንተ ነው” አለው። ጺባም “ንጉሥ ሆይ! እነሆ እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ ዘወትር አንተን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ለመሥራት እተጋለሁ!” ሲል መለሰ።


ለመሆኑ ይህን ወይም ያንን ስጡኝ፥ ወይም በሀብታችሁ ታደጉኝ ብያችኋለሁን?


ነገር ግን ያ አገልጋይ ‘ጌታዬ ቶሎ አይመጣም፤ ይዘገያል’ ብሎ በማሰብ እየበላ፥ እየጠጣ፥ እየሰከረም ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን መምታት ይጀምራል።


አንድ ቀን ሞአባዊትዋ ሩት ናዖሚን “በፊቱ ሞገስ ወደማገኝበት ሰው እርሻ ሄጄ ቃርሚያ ልቃርም” አለቻት። ናዖሚም “ልጄ ሆይ! ሂጂ!” አለቻት።


እርስዋም “እኔን አገልጋይህን በጸሎትህ አስበኝ!” አለችው፤ ከዚያም ተነሥታ በመሄድ ምግብ ተመገበች፤ ሐዘንዋንም አቆመች።


跟着我们:

广告


广告