Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 32:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ‘በተለይም አገልጋይህ ያዕቆብ ከበስተኋላ እየመጣ ነው’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው። ይህንንም ያለበት ምክንያት “እኔ ከመድረሴ በፊት በሚደርስለት ስጦታ ቊጣውን አበርድ ይሆናል፤ በኋላም በማገኘው ጊዜ በደስታ ይቀበለኛል” በሚል ሐሳብ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በተለይም ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ ማለትን አትዘንጉ።” ይህንም ያዘዘው፣ “ዔሳው ከእኔ ጋራ ከመገናኘቱ በፊት እጅ መንሻዬ አስቀድሞ ቢደርሰው ምናልባት ልቡ ይራራና በሰላም ይቀበለኛል” ብሎ ስላሰበ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ‘እንዲሁም ባርያህ ያዕቆብ ከኋላችን ነው’ እንድትሉት። እሱ ‘በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፥ ከዚያም በኋላ ምናልባት ይቀበለኛል ፊቱንም አያለሁ’ ብሎ አስቧል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እን​ዲ​ህም በሉ፦ እነሆ አገ​ል​ጋ​ይህ ያዕ​ቆብ ከኋ​ላ​ችን ነው። በፊቴ በሚ​ሄ​ደው እጅ መንሻ እታ​ረ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ምና​ል​ባት ይራ​ራ​ል​ኛል፤ ፊቱ​ንም አያ​ለሁ ብሎ​አ​ልና።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እንዲህም በሉት፦ እነሆ ባሪያህ ያዕቆብ ከኍላችን ነው። በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፤ ከዚያም በኍላ ምናልባት ይራራልኛል ፊቱንም አያለሁ ብሎአልና።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 32:20
14 交叉引用  

ለሁለተኛውም ለሦስተኛውም ክፍል እረኞችና ለቀሩትም የመንጋ ጠባቂዎች “እናንተም ዔሳውን ስታገኙት እንደዚሁ ንገሩት፤


በዚህ ዐይነት ስጦታውን አስቀድሞ ከላከ በኋላ፥ እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ዐደረ።


አባታቸው ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ መሄዳችሁ የማይቀር ከሆነ ለአገረ ገዢው ገጸ በረከት የሚሆን ምድራችን ከምታፈራው ምርጥ ነገር ሁሉ በስልቻዎቻችሁ ጨምራችሁ ሂዱ፤ ይኸውም በለሳን፥ ማር፥ ቅመማ ቅመም፥ ከርቤ፥ ተምርና ለውዝ ይዛችሁ ሂዱ።


ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖችም ወደ እርሱ ቀርበው “የእስራኤል ነገሥታት ምሕረት አድራጊዎች መሆናቸውን ሰምተናል፤ ስለዚህ በወገባችን ማቅ ታጥቀን፥ በራሳችንም ገመድ ጠምጥመን ወደ እስራኤል ንጉሥ ዘንድ ሄደን ምሕረት እንድንጠይቀው ፍቀድልን፤ ምናልባትም ሕይወትህን ያተርፍ ይሆናል” አሉት።


ቊጣ ጭቅጭቅን ያነሣሣል፤ ትዕግሥት ግን ጠብን ያበርዳል።


የንጉሥ ቊጣ የሞት መልእክተኛ ነው። ብልኅ ሰው ግን ቊጣውን ያበርዳል።


ስጦታ ለሰጪው መንገድን ይከፍትለታል፤ ወደ ትልልቆች ሰዎችም ፊት መቅረብ ያስችለዋል።


የተቈጣ ሰው ስጦታ በድብቅ ሲቀርብለት ንዴቱ ይበርድለታል፤ በምሥጢር የሚሰጥ እጅ መንሻ ቊጣን ያበርዳል።


ምንም ዐይነት ካሳ መቀበል አይፈልግም፤ የስጦታም ብዛት ቊጣውን አያበርድለትም።


እኛ ከጥፋት እንድንድን ምናልባት እግዚአብሔር ራርቶልን ከሚያስፈራው ቊጣው ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”


እርሱ የሚቃወሙትን ሰዎች በገርነት የሚያርም መሆን አለበት፤ ምናልባትም እውነትን ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ንስሓ የመግባትን ዕድል ይሰጣቸው ይሆናል።


አገራችሁን ለማጥፋት በተላኩት አይጦችና እባጮች አምሳል እነዚህን ስጦታዎች ሠርታችሁ ለእስራኤል አምላክ ክብር መስጠት አለባችሁ፤ ይህን ብታደርጉ ምናልባት እናንተን፥ አማልክታችሁንና ምድራችሁን የሚቀጣበትን መቅሠፍት ያነሣ ይሆናል፤


跟着我们:

广告


广告