ዘፍጥረት 32:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 እኔ ባሪያህ እስካሁን ላደረግህልኝ ቸርነትና ታማኝነት ብቁ አይደለሁም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር በእጄ ላይ ከነበረው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ሰራዊት ሆኛለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ለባርያህ ካሳየኸው ከጽኑ ፍቅርና ከታማኝነትህ ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፥ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበር፥ አሁን ግን ለሁለት ወገን የተከፈልኩ ሆንሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ለባሪያህ በአደረግኸው በምሕረትህና በእውነትህም ሁሉ በጎውን አድርግልኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ለባሪያህ ከሠራኸው ከምሕረትህን ከእውነትህም ሁሉ ትንሽ ስ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ። 参见章节 |