ዘፍጥረት 30:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም41 ጤናማና ብርቱ የሆኑት መንጋዎች ፍትወት እየተሰማቸው ሲጐመዡ ያዕቆብ በትሮቹን በፊታቸው ባሉት ውሃ መጠጫዎች ውስጥ ያኖራቸው ነበር፤ በዚህ ዐይነት በትሮቹን እያዩ ይፀንሱ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም41 ያዕቆብም ብርቱ እንስቶች አውራ ፈልገው በሚቅበጠበጡበት ጊዜ፣ በትሮቹ አቅራቢያ እንዲጠቁ በትሮቹን በውሃ ገንዳዎቹ ውስጥ ፊት ለፊታቸው ያስቀምጥ ነበር፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)41 እንዲህም ሆነ፥ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ፥ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)41 እንዲህም ሆነ፦ በጎቹ በሚፀንሱበት ወራት በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በበጎቹ ፊት በውኃ ማጠጫ ገንዳው ውስጥ ያኖራቸው ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)41 እንዲህም ሆነ፤ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ፤ 参见章节 |