Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 30:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ነገር ግን በዚያኑ ቀን ላባ ሸመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቊጣ ያለባቸውን ወንዶች ፍየሎችና ዝንጒርጒር የሆኑትን ነጭ ነጠብጣብ ያለባቸውን ሴቶች ፍየሎች መረጠ፤ እንዲሁም ጥቊር የሆኑትን በጎች ለየና ልጆቹ እንዲጠብቁአቸው አደረገ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ነገር ግን በዚያ ዕለት ከተባዕት ፍየሎች ሽመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቍጣ ያለባቸውን ሁሉ፣ እንዲሁም ከእንስት ፍየሎች ነቍጣ ያለባቸውን ዝንጕርጕር የሆኑትን ሁሉ፣ ማንኛውንም ነጭ ያለበትን ሁሉ መረጠ፤ ደግሞም ጥቋቍር የሆኑትንም በጎች ሁሉ ለየና ወንዶች ልጆቹን አስጠበቃቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 በዚያም ቀን ከተባዕቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቁጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹም ፍየሎች ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸውን፥ ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ፥ ከበጎቹም መካከል ጥቁሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 በዚ​ያም ቀን ከተ​ባ​ቶቹ ፍየ​ሎች ሽመ​ል​መሌ መሳ​ይና ነቍጣ ያለ​ባ​ቸ​ውን፥ ከእ​ን​ስ​ቶቹ ፍየ​ሎች ዝን​ጕ​ር​ጕ​ርና ነቍጣ ያለ​ባ​ቸ​ውን፥ ነጭ ያለ​በ​ትን ማን​ኛ​ው​ንም ሁሉ፥ ከበ​ጎ​ቹም መካ​ከል ጥቁ​ሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለል​ጆቹ ሰጣ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 በዚያም ቀን ከተባቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቍጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹም ፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸውን ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ ከበጎቹም መካከል ጥኩሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 30:35
5 交叉引用  

ዛሬ በመንጋዎችህ መካከል ልለፍና ዝንጒርጒርና ነቊጣ፥ ጥቊርም የሆኑትን በጎች ሁሉ ልለይ፤ እንዲሁም ነቊጣና ዝንጒርጒር የሆኑትን ፍየሎች እመርጣለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ፤


ላባም “እሺ አንተ ባልከው እስማማለሁ” አለ።


ከዚህ በኋላ ላባ መንጋውን ነድቶ የሦስት ቀን መንገድ ያኽል ከያዕቆብ ርቆ ሄደ፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን መንጋዎች መጠበቁን ቀጠለ።


እግዚአብሔር የአባታችሁን የላባን መንጋዎች ወስዶ ለእኔ የሰጠኝ በዚህ ዐይነት ነው።


‘እኛ ልክ እንደ ቀድሞ አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ የምንተዳደረው በግ በማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። በግ አርቢዎች በግብጻውያን ዘንድ የተናቁ ስለ ሆኑ ይህን በመናገር በጌሴም ምድር ለመኖር ፈቃድ ታገኛላችሁ።”


跟着我们:

广告


广告