Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 30:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ልያም “እጅግ ደስ ብሎኛል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ሴቶች ሁሉ ‘ደስተኛዋ ሴት!’ ይሉኛል” ስትል ስሙን አሴር ብላ ጠራችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ልያም፣ “ምንኛ ደስተኛ ሆንሁ ከእንግዲህ ሴቶች ደስተኛዋ ይሉኛል” አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ አወጣችለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ልያም፦ ደስታ ሆነልኝ፥ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች፥ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ልያም፥ “እኔ ብፅ​ዕት ነኝ፤ ሴቶች ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ኛ​ልና” አለች፤ ስሙ​ንም አሴር ብላ ጠራ​ችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ልያም፦ ደስታ ሆነልኝ፤ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 30:13
8 交叉引用  

የልያ አገልጋይ ዚልፋ ለያዕቆብ ሌላ ወንድ ልጅ ወለደችለት።


የልያ አገልጋይ የነበረችው የዚልፋ ልጆች ጋድና አሴር ናቸው። እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በመስጴጦምያ ሳለ የተወለዱለት ናቸው።


የአሴር ልጆች፦ ይምና፥ ይሽዋ፥ ይሽዊና በሪዓ ናቸው። እኅታቸው ሤራሕ ትባላለች። የበሪዓ ልጆች ደግሞ ሔቤርና ማልኪኤል ናቸው።


“አሴር ከምድሩ ብዙ ሀብት አግኝቶ ይበለጽጋል፤ በነገሥታት ፊት መቅረብ የሚችል ጥሩ ምግብ ያዘጋጃል።


ልጆችዋ አድናቆታቸውን ይገልጡላታል፤ ባልዋም ያመሰግናታል፤


እኔ ግን የምወደው አንዲትዋን ብቻ ነው፤ እርስዋም ምንም እንከን የሌለባት እንደ ርግብ የተዋበች ናት፤ እርስዋ ለእናትዋ አንድ ናት፤ የወለደቻት እናትዋም ከሁሉ አብልጣ ታፈቅራታለች፤ ቈነጃጅትም እርስዋን እየተመለከቱ ያወድሱአታል፤ ነገሥታትና የንጉሥ ቊባቶች ያሞግሡአታል።


እግዚአብሔር እኔን ዝቅተኛ አገልጋይቱን ተመልክቶአልና፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ የተባረክሽ ነሽ ይሉኛል፤


跟着我们:

广告


广告