Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 አዳምም “በአትክልቱ ቦታ ውስጥ የአንተን ድምፅ ሰማሁ፤ እራቁቴንም ስለ ሆንኩ በመፍራት ተደበቅሁ” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አዳምም፣ “ድምፅህን በአትክልቱ ስፍራ ሰማሁ፤ ዕራቍቴን ስለ ሆንሁ ፈራሁ፤ ተሸሸግሁም” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እርሱም፥ “በገነት ድምጽህን ሰማሁ፥ ዕራቁቴንም ስለ ሆንኩ ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም።” አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አዳ​ምም አለ፥ “በገ​ነት ስት​መ​ላ​ለስ ድም​ፅ​ህን ሰማሁ፤ ዕራ​ቁ​ቴ​ንም ስለ​ሆ​ንሁ ፈራሁ፤ ተሸ​ሸ​ግ​ሁም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እርሱም አለ፦ በገነት ድምጽህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፤ ተሸሸግሁም።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 3:10
17 交叉引用  

አዳምና ሚስቱ ራቊታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አያፍሩም ነበር።


እግዚአብሔርም “እራቁትህን እንደ ሆንክ ማን ነገረህ? አትብላ ካልኩህ ዛፍ ፍሬ ወስደህ በላህን?” አለው።


የሁለቱም ዐይኖች ተከፍተው እራቁታቸውን እንደ ሆኑ ተገነዘቡ፤ ስለዚህ የበለስ ቅጠሎችን አገናኝተው ሰፉና በማገልደም እርቃናቸውን ሸፈኑ።


ስለዚህ በእርሱ ፊት መቆም እጅግ ያስፈራኛል፤ ይህን ባሰብኩ ጊዜ እንኳ ፈራሁ።


“በደሌን በውስጤ አልሸሸግሁም እንደ ሌሎች ሰዎች ኃጢአቴንም አልሰወርኩም።


አንተን ከመፍራቴ የተነሣ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርድህንም እጅግ ፈራሁት።


ሕዝቡም የነጐድጓዱንና የእምቢልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ እንዲሁም መብረቁ ሲብለጨለጭና ተራራው ሲጤስ ባዩ ጊዜ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ርቀው ቆሙ፤


እነርሱም ሙሴን “አንተ ተናገረን፤ እናዳምጥሃለን፤ እግዚአብሔር ቢናገረን ግን እንሞታለን ብለን እንፈራለን” አሉት።


እኔ የቀድሞ አባቶችህ የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤” በዚህ ጊዜ ሙሴ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ማየት ስለ ፈራ ፊቱን ሸፈነ።


አሮን ሕዝቡን በጠላቶቻቸው ፊት መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ መረን እንደ ለቀቃቸው ሙሴ ተመለከተ።


በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ይፈራሉ፤ ከሐዲዎችም ይርበደበዳሉ፤ ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳትና ከዘለዓለማዊ ነበልባል ጋር ለመኖር የሚችል ማነው ይላሉ።


ሕዝብ ሁሉ ተራቊተሽ ያዩሻል፤ ኀፍረትሽ ይጋለጣል፤ እኔ ማንንም ሳልምር ሁሉን እበቀላለሁ።”


“እኔን ባለማስታወስና ስለ እኔ ባለማሰብ ውሸት የተናገራችሁት ማንን ፈርታችሁ ነው? እኔን ያልፈራችሁኝ ለብዙ ጊዜ ዝም ስለልኩና እንዳላየ ስለሆንኩ ነውን?


ነገር ግን ያ ብርቱ እሳት ያጠፋናል፤ ታዲያ ለምን መሞት እንፈልጋለን? እግዚአብሔር አምላካችን እንደገና ቢናገረን እንሞታለን።


በዚህ በኩል ልባችን ቢወቅሰንም እግዚአብሔር ከልባችን በላይ ነው፤ እርሱም ሁሉን ነገር ያውቃል።


“እነሆ! እኔ እንደ ሌባ በድንገት እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይሆንና ኀፍረቱን ሰዎች እንዳያዩበት ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው የተመሰገነ ነው!”


跟着我们:

广告


广告