Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 29:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እንደገና ፀነሰችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እግዚአብሔር እንዳልተወደድኩ ሰማ፤ ይህንንም ልጅ ደግሞ ሰጠኝ” ስትል ስሙን ስምዖን አለችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እንደ ገናም ፀንሳ ወለደች፤ እርሷም “እግዚአብሔር እንዳልተወደድኩ ሰምቶ ይህን ልጅ በድጋሚ ሰጠኝ” አለች። ከዚያም የተነሣ ስምዖን ብላ ጠራችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ደግሞም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ሰማ ይህን ደገመኝ አለች፥ ስሙንም ስምዖን ብላ ጠራችው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ልያም ዳግ​መኛ ፀነ​ሰች፤ ሁለ​ተኛ ወንድ ልጅ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደ​ች​ለት፤ “እኔ እንደ ተጠ​ላሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሰማ ይህን ጨመ​ረ​ልኝ” አለች፤ ስሙ​ንም ስም​ዖን ብላ ጠራ​ችው ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ደግሞም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች፤ እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ስማ ይህን ደገመኝ አለች ስምዖን ብላ ጠራችው

参见章节 复制




ዘፍጥረት 29:33
12 交叉引用  

ልያም “አገልጋዬን ለባሌ በመስጠቴ እግዚአብሔር ደመወዜን ከፈለኝ” ስትል ይሳኮር ብላ ጠራችው፤


እርስዋም “እግዚአብሔር መልካም ስጦታ ሰጠኝ፤ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ያከብረኛል” ስትል ስሙን ዛብሎን ብላ ጠራችው።


ራሔልም “እግዚአብሔር ፈረደልኝ፤ ጸሎቴንም ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጠኝ” አለች፤ በዚህም ምክንያት ስሙን ዳን ብላ ጠራችው።


ራሔልም “ከእኅቴ ጋር ብርቱ ትግል ታግዬ አሸነፍኳት” አለች፤ ስለዚህ ስሙን ንፍታሌም ብላ ጠራችው።


በሦስተኛው ቀን ሰዎቹ ገና ከመገረዝ ቊስል ሳይድኑ ከያዕቆብ ልጆች መካከል ሁለቱ የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊ ሰይፍ፥ ሰይፋቸውን ይዘው ማንም ሳያውቅባቸው፥ ወደ ከተማ ገቡና ወንዶቹን ሁሉ ገደሉ።


ያዕቆብ ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፤ “በእኔ ላይ ከባድ ችግር አመጣችሁብኝ፤ እነሆ በዚህ ድርጊት የተነሣ በዚህች ምድር የሚኖሩ ከነዓናውያንና ፈሪዛውያን ይጠሉኛል፤ እኛ በቊጥር አነስተኞች ነን፤ እነርሱ ተባብረው ቢያጠቁን እኔና ቤተሰቤ እንጠፋለን።”


የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮርና ዛብሎን ናቸው።


ዮሴፍ ከእነርሱ ነጠል ብሎ አለቀሰ፤ እንደገናም ወደ እነርሱ ተመልሶ አነጋገራቸውና ስምዖንን ከመካከላቸው ወስዶ በፊታቸው አሰረው።


ስምዖን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከብንያም ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤


ከስምዖን ነገድ የአሚሁድ ልጅ ሰላሚኤል፥


“አንድ ሰው ሁለት ሚስቶችን አግብቶ አንደኛይቱን አፍቅሮ ሌላይቱን ባያፈቅርና ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ቢወልዱለት፥ ምናልባት የመጀመሪያው ልጅ የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን፥


跟着我们:

广告


广告