ዘፍጥረት 28:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 አይዞህ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበትም ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህም ምድር በደኅና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈጽምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የሰጠሁህን ተስፋ እስከምፈጽምልህ ድረስ አልተውህም።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፥ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 እነሆም፥ እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ በምትሄድበትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚያችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ በምትሄድባትም ምድር እመልስሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድርስ አልተውህምና። 参见章节 |