Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 27:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 በሰይፍህ ኀይል ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ፤ በተቃወምከው ጊዜ ግን ከእርሱ ጭቈና ትላቀቃለህ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 በሰይፍ ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ። አምርረህ በተነሣህ ጊዜ ግን፣ ቀንበሩን ከጫንቃህ ላይ፣ ወዲያ ትጥላለህ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 በሰይፍህም ትኖራለህ፥ ለወንድምህም ትገዛለህ፥ ነገር ግን በተቃወምኸው ጊዜ ቀንበሩን ከአንገትህ ትጥላለህ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 በሰ​ይ​ፍ​ህም ትኖ​ራ​ለህ፤ ለወ​ን​ድ​ም​ህም ትገ​ዛ​ለህ፤ ነገር ግን ቀን​በ​ሩን ከአ​ን​ገ​ትህ ልት​ጥል ብት​ወ​ድድ ከእ​ርሱ ጋር ተስ​ማማ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 በሰይፍህም ትኖራለህ፥ ለወንድምህም ትገዛለህ ነገር ግን በተቃወምኸው ጊዜ ቀንበሩን ከአንገትህ ትጥላለይ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 27:40
17 交叉引用  

እግዚአብሔርም፥ “በማሕፀንሽ ያሉት ሁለት ሕዝቦች ናቸው፤ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ሁለት ወገኖች ትወልጃለሽ፤ አንዱም ከሌላው የበረታ ይሆናል፤ ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል” አላት።


መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ያገልግሉህ፤ በወንድሞችህ ሁሉ ላይ አለቃ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚመርቁህም የተመረቁ ይሁኑ።”


መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው መጡና “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ከአንተ ጋር ለመገናኘት በመምጣት ላይ ነው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ” አሉት።


ዔሳውም “ወንድሜ ሆይ፥ እኔ በቂ ሀብት አለኝ፤ የአንተ ለራስህ ይሁን” አለው።


በመላው ኤዶም ብዙ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የእርሱ ተገዢዎች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።


አሜስያስ ሆይ! እነሆ፥ አንተም ኤዶማውያንን ድል ስላደረግህ ልብህ በትዕቢት ተሞልቶአል፤ በአገኘኸውም ድል በመደሰት ዐርፈህ በቤትህ ብትቀመጥ ይሻልሃል፤ በአንተና በሕዝብህ ላይ መቅሠፍትን የሚያስከትል ነገር ለመቈስቈስ ስለምን ትፈልጋለህ?”


አሜስያስ “የጨው ሸለቆ” እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ዐሥር ሺህ የሚሆኑ የኤዶም ወታደሮችን ፈጀ፤ ሴላዕ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ይዞ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት፤ እስከ አሁንም በዚሁ ስም ትጠራለች።


ንጉሥ ኢዮራም የቀድሞ አባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ስለ ተወ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኤዶም ከይሁዳ በመገንጠል ነጻ መንግሥት ሆነች፤ በዚሁ ወቅት የሊብና ከተማም በይሁዳ ላይ ዐመፀች፤


በኢዮራም ዘመነ መንግሥት ኤዶም በይሁዳ ላይ ዐምፆ የራሱን ነጻ መንግሥት አቋቋመ፤


ሞአብ መታጠቢያዬ ነው፤ ኤዶም የእኔ መሆኑን ለማረጋገጥ ጫማዬን አኖርበታለሁ፤ በፍልስጥኤማውያንም ላይ።”


እኔ የመጣሁት፥ ሰላምን በምድር ላይ ለማምጣት አይምሰላችሁ፤ እኔ ጦርነትን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም።


跟着我们:

广告


广告